ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ከ10 አመት በፊት የተያዘችውን ክሪሚያን ለማስመለስ ውጊያ መደረግ አለበት አሉ
ሩሲያ ክሪሚያን የተቆጣጠረችው በፈረንጆቹ 2014 ነበር
ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ዩክሬን እና አለምአቀፍ አጋሮቿ ክሬሚያን ለማሰመለስ ውጊያ ማካሄድ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ከ10 አመት በፊት የተያዘችውን ክሪሚያን ለማስመለስ ውጊያ መደረግ አለበት አሉ።
ኪቭ ሩሲያ የጥቁር ባህሯን ባህረሰላጤ የወረረችበትን 10ኛ አመት በትናንተናው እለት ስታስብ፣ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ዩክሬን እና አለምአቀፍ አጋሮቿ ክሬሚያን ለማሰመለስ ውጊያ ማካሄድ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።
ሩሲያ ክሪሚያን የተቆጣጠረችው በፈረንጆቹ 2014 ነበር። ሩሲያ የካቲት ወር 2022 በዩክሬን ላይ አጠቃላይ ጦርነት ስትጀምር ክሪሚያን እንደመስፈንጠሪያ ተጠቅማለች።
ፕሬዝደንቱ ባሰሙት የቪዲዮ ንግግር ሩሲያ እንዲህ አይነቱን አስከፊ ጦርነት የከፈተችው ዓለም ትኩረት አልሰጠውም የሚል ስሜት ስላደረባት ነው ብለዋል።
ሩሲያ ክሬሚያን ወደ ግዛቷ የጠቀለለችው በሩሲያ የሚደገፉ ተገንጣይ ቡድኖችን ተጠቅማ ነበ
በወቅቱ ይህን ድርጊት አለምአቀፉ ማህበረሰብ ህገወጥ ነው በሚል ማውገዙ ይታወሳል።
ክሬሚያን በሞስኮ በተደረገ ስምምነት በይፋ ወደ ሩሲያ የተቀላቀለችበት ቀን በየአመቱ በመጋቢት 18 ይከበራል።
የሩሲያ ወታደሮች ለቀው እንዲወጡ የዲፕሎማሲ ጫና እያሳደረች ያለችው ኪቭ በ1991 የነበረው ድንበሯ እስኪመለስ ድረስ መዋጋቷን እንደምትቀጥል ገልጻለች።
የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ከተጀመረ ሶስተኛ አመቱን የያዘ ሲሆን ዩክሬን ረጅም ርቀት በሚሸፍነው ግንባር የሩሰያን ጥቃት ለመከላከል እየሞከረች ነው።
በቅርቡ አብዲቪካ ከተማን የተቆጣጠረችው ሩሲያ ወደፊት እንደምትገፋ መግለጿ ይታወሳል።