በሩሲያ ውስጥ የሰፈሩት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ቁጥር ወደ 100ሺ ሊያድግ እንደሚችል ዘለንስኪ ተናገሩ
ኪቭ እና ምዕራባውያን አጋሮቿ ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ በዩክሬን የምታደርገውን ጦርነት ለማጠናከር የሰው ኃይል እና የጦር መሳሪያ ድጋፍ እየሰጠች ነው ይላሉ
ፕሬዝደንት ባይደን ዩክሬን አሜሪካ የሰጠቻትን የረጅም ርቀት ሚሳይሎችን ሩሲያ ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እንድትመታ ፈቅደዋል ተብሏል
በሩሲያ ውስጥ የሰፈሩት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ቁጥር ወደ 100ሺ ሊያድግ እንደሚችል ዘለንስኪ ተናገሩ።
ሩሲያ ውስጥ በተጠባባቂነት የሰፈሩ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ቁጥር ወደ 100ሺ ሊያድግ እንደሚችል የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
ኪቭ እና ምዕራባውያን አጋሮቿ ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ በዩክሬን የምታደርገውን ጦርነት ለማጠናከር የሰው ኃይል እና የጦር መሳሪያ ድጋፍ እየሰጠች ነው ይላሉ።
"አሁን ፑቲን 11ሺ ወታደሮችን አምጥቷል። ይህ ኃይል ወደ 100ሺ ሊያድግ ይችላል" ብለዋል ዘለንስኪ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ባደረጉት ንግግር።
የደቡብ ኮሪያ የስለላ ድርጅት ባለፈው ሳምንት እንደገለጸው የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከዩክሬን ኃይሎች ጋር ውጊያ ማድረግ ጀምረዋል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ሐምሌ ወር ሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ በፒዮንግያንግ በደረሱበት ወታደራዊ ስምምነት ላይ በዚህ ወር ፊርማቸውን በማኖር ህግ እንዲሆን አድርገዋል።
ስምምነቱ ሀገራቱ ጥቃት በሚደርስባቸው ወቅት አንደኛው ለሌላኛው ሁሉንም አይነት አማራጭ በመጠቀም በአፋጣኝ ድጋፍ ለማድረግ ያስችላል።
ፕሬዝደንት ባይደን ዩክሬን አሜሪካ የሰጠቻትን የረጅም ርቀት ሚሳይሎችን ሩሲያ ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እንድትመታ ፈቅደዋል ተብሏል።
ዩክሬን ለረጅም ጊዜ ስታቀርበው የነበረው ጥያቄ ምላሽ ቢያገኝም፣ በሩሲያ በኩል የአጸፋ ምላሽ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
ፑቲን በአዲሱ የሩሲያ የኑክሌር አጠቃቀም መመሪያ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን በትናንትናው እለት በመፈረም ውጥረቱን ከፍ አድርገውታል።