ዘለንስኪ በሀገር ውስጥ የተሰራውን ድሮን ሚሳይል ይፋ አደረጉ
ዘለንስኪ የሩሲያውን ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንን "የሬድ ስኩየሩ ያረጀ ሰው" ሲሉ በንቀት ጠርተዋቸዋል
ዘለንስኪ አዲሱ የጦር መሳሪያ ዩክሬን ከዚህ በፊት ከሰራቻቸው ድሮኖች ጋር ሲነጻጸር ኃይለኛ እና ፈጣን ነው ብለዋል
ዘለንስኪ በሀገር ውስጥ የተሰራውን ድሮን ሚሳይል ይፋ አደረጉ።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጦርነቱን ወደ ሩሲያ ግዛት ለመውሰድ ይረዳል ያሉትን በሀገር ውስጥ የተሰራውን የድሮን ሚሳይል በትናንትናው እለት ይፋ አድርገዋል።
ዘለንስኪ የሩሲያውን ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንን "የሬድ ስኩየሩ ያረጀ ሰው" ሲሉ በንቀት ጠርተዋቸዋል።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ዩክሬን ከሶቬት ህበረት ነጻ የወጣችበትን 33ኛ አመት እያከበረች ባለችበት ወቅት ባስሙት ንግግር ፓሊያንይሲያ የተባለው አዲሱ የጦር መሳሪያ ዩክሬን ከዚህ በፊት ከሰራቻቸው እና ሩሲያን እየተዋጋች ከለችባቸው ድሮኖች ጋር ሲነጻጸር ኃይለኛ እና ፈጣን ነው ብለዋል።
"ጦላቶቻችን በምን መልኩ እንደምንበቀላቸው ያውቃሉ። ትርጉም ያለው፣ ተመሳሳይ እና የረጅም ርቀት ነው"።
ዘለንስኪ አዲሶቹ የዩክሬን የጦር መሳሪያዎች ዩክሬን ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን በተሳካ ሁኔታ ለመምታት ጥቅም ላይ ውለዋል ብለዋል።
ፕሬዝደንቱ የ71 አመቱን የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑንን እና ከሞስኮ የሚሰማውን የኑክሌር ማስፈራሪያ ለመግለጽ የንቀት ቋንቋ ተጠቅመዋል።
ዘለንስኪ "እያንዳንዱን ሰው የኑክሌር ቀልፍ እጫናለሁ እያለ የሚያስፈራራው የሬድ ስኩየሩ (የቀዩ አደባባይ) ሽማግሌ ስለየትኛውም ቀይ መስመር እኛን ሊያዘን አይችልም" ሲሉ በቴሌግራም በተላለፈ የቪዲዮ መልእክት ተናግረዋል።
ከፈረንጆቹ የካቲት 2022 ጀምሮ በብዙ ሽዎች በሚቆጠሩ ሚሳይሎች እያጠቃች ያለችው ሩሲያ ዩክሬን የፈጸመችውን የድሮን ጥቃት ሽብር ስትል ገልጻዋለች። የሞስኮ ወታደሮች በዩክሬን ምስራቃዊ ክፍል ወደፊት እየገፉ ሲሆን እስካሁን 18 በመቶ የሚሆነውን የዩክሬን ግዛት ተቆጣጥረዋል።
ዘለንስኪ የኪቭ አጋሮች የምዕራባውያን መሳሪያዎችን ሩሲያ ግዛት ውስጥ ዘልቆ በመግባት ሩሲያ ዩክሬይንን ለማጥቃት የምትጠቀምባቸው አውሮፕላኖች ያረፉባቸውን የአየር ጦር ሰፈሮች እንድትመታባቸው እንዲፈቅዱላቸው እየጠየቁ ናቸው።
ፕሬዝደንቱ በአዲሱ የጦር መሳሪያ ለማጥቃት ብንወስንም፣ የተወሰኑ አጋሮቻቸውን አልፈቀዱልንም ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
ዩክሬን በሩሲያ ላይ መብረቃዊ ድንበር አቋራጭ ጥቃት መክፈቷን ተከትሎ አድናቆታቸውን ለመግለጽ ለዋና የጦር አዛዡ ኦሌክሳንደር ሲይርስኪ የጀነራልነት ማዕረግ ሰጥተዋል።
ዩክሬን በሩሲያ ኩርስክ ግዛት ጥቃት በክፈት የሩሲያን የማጥቃት እንቅስቃሴ ለማዛባት አስባ የነበረ ቢሆንም የሩሲያ ኃይሎች ወደፊት እየገፉ ነው ተብሏል።