ዘለንስኪ ዩክሬን የአየር መከላከያ ሚሳይል እያለቀባት ነው ሲሉ አስጠነቀቁ
ዘለንስኪ ዩክሬን 25 አሜሪካ ሰራሽ የሆኑ የፓትሪዎት ዲፌንስ ሚሳይል ስርአት ያስፈልጓታል ብለዋል
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ሩሲያ የጀመረችውን የረጅም ርቀት የሚሳይል ጥቃት የምትቀጥል ከሆነ ዩክሬን የመከላከያ ሚሳይል ሊያልቅባት ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል
ዘለንስኪ ዩክሬን የአየር መከላከያ ሚሳይል እያለቀባት ነው ሲሉ አስጠነቀቁ።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሩሲያ የጀመረችውን የረጅም ርቀት የሚሳይል ጥቃት የምትቀጥል ከሆነ ዩክሬን የመከላከያ ሚሳይል ሊያልቅባት ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ዘለንስኪ ይህን ማስጠንቀቂያ ያቀረቡት ሩሲያ ለሳምንታት ያለማቋረጥ ያደረሰችውን ጥቃት ተከትሎ የዩክሬን የአየር መከለከያ ሚሳይል ክምችት እየቀነሰ በምጣቱ ነው።
ፕሬዝደንቱ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ማስተላለፉት መልእክት "ሩሲያ ባለፈው ወር እንዳደረገችው አሁንም ዩክሬንን መምታቷን ከቀጠለች የመከላከያ ማሳይሎች ሊያልቁብን ይችላሉ፤ አጋሮቻችንም ያውቁታል" ብለዋል።
አጋሮቻቸው የአየር መከላከያ ሚሳይል እንዲረዷቸው የተማጸኑት ዘለንስኪ ዩክሬን ለአሁኑ ግን በቂ የሚባል ክምችት እንዳላት ዘለንስኪ ተናግረዋል።
ዘለንስኪ ዩክሬን 25 አሜሪካ ሰራሽ የሆኑ የፓትሪዎት ዲፌንስ ሚሳይል ስርአት ያስፈልጓታል ብለዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያደረሰች ያለውን መጠነሰፊ ጥቃት የቀጠለች ሲሆን በትናንትው እለት ባደረሰችው ሁለት የድሮን ጥቃቶች ስምንት ስዎች ሲገደሉ 10 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በሩሲያ በዩክሬን የኃይል መሰረት ልማት ላይ ባደረሰችው ጥቃት ምክንያት ግዙፉ የግል የኃይል ኩባንያ ዲቴክ 80 በመቶ የማመንጨት አቅሙን አጥቷል።
በቅርቡ በምስራቅ ዩክሬን ተጨማሪ ቦታዎች የያዘችው ሩሲያ በከፊል የያዘቻቸውን አራት ግዛቶች ሙሉ በሙሉ ለመቅጣጠር ማጥቃቷን እንደምትቀጥል ገልጻለች።
ዩክሬን በግንባር ያሉ ቦታዎችን የለቀቀችው የምዕራባውያን ወታደራዊ ድጋፍ በበፍጥነት ባለመድረሳቸው እንደሆነ መግለጿ ይታወሳል።