የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት አሜሪካ ከሀገር እንዲወጡ ያቀረበችላቸውን ጥያቁ ውድቅ አድረጉ
ፕሬዝዳንቱ “ብቻችንን አጋፍጠውናል” ሲሉ ምዕራባውያንን መውቀሳቸው ይታወሳል
ፕሬዝዳንት ዝሌንስኪ "ጦርነቱ እዚህ ነው፤ እኔ ምፈልገው የማምለጫ መንገድ ሳይሆን የጦር መሳሪያ ነው” ብለዋል
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቭሎይድሜር ዘለንስኪ አሜሪካ ከሀገር እንዲወጡ ድጋፍ ለማድረግ ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ፕሬዝዳንት ቭሎይድሜር ዘለንስኪ፤ “ጦርነቱ እየተካሄደ ያለው እዚህ ነው፤ እኔ የማምለጫ መንገድ ሳይሆን የጦር መሳሪያ ነው የምፈልገው” ማለታቸውን የአሜሪካ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ዋሽንግተን ፖስት የአሜሪካ እና የዩክሬን ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ ባወጣው ዘገባ፤ የአሜሪካ መንግስት ፕሬዝዳንት ቭሎይድሜር ዘለንስኪ ከዩክሬን የሚወጡበት መንገድ ላይ እገዛ ለማድረግ ተዘጋጇል።
የአሜሪካን ከሀገር እናስወጣ ጥያቅ ውድቅ ያደረጉት ፕሬዝዳንት ቭሎይድሜር ዘለንስኪ በማህበራዊ ትስስር ገጸች ላይ አድናቆት እየቀረበላቸው ነው ተብሏል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቭሎይድሜር ዘለንስኪ ዛሬ ጠዋት ላይ በኬቭ ከተማ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ የሚያሳይ ቪዲዮ መልቀቃቸው ተነግሯል።
በለቀቁት ተንቀሳቃሽ ምስልም፤ ለዪክሬን ጦር እጅ ስጡ በሚል ትእዛዝ ተላልፏል የሚባለው ሀሰት ነው ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ በዛሬ ጠዋት መልእከታቸው፤ “ሁልችሁም ዩክሬናውያን እንዴት አደራችሁ፤ “ጦራችን እጅ እንዲሰጥ ጥሪ ያስተላለፍኩ በማስበሰል በርካታ የሀሰት መረጀዎች እየወጡ ነው” ብለዋል።
“አድምጡኝ እኔ እዚሁ ነው ያለሁት፤ ትጥቃችንን አንፈታም፣ ሀገራችንን እንከላከላለን” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ “የኛ መሳሪያ እውነታችን፣ ሀገራችን፣ መሬታችን እና ቤተሰባችን ነው፤ ይህንን ሁሉ እንከላከላለን” ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ቭሎይድሜር ዘለንስኪ በትናነትናው እለት በሰጡት መግለጫ፤ “ብቻችንን አጋፍጠውናል” ሲሉ ምዕራባውያንን መውቀሳቸው ይታወሳል።
“ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደተወን ነው የተሰማኝ፤ እንደሚደግፉን ነበር ቃል ሲገቡልን የነበሩት፤ ሆኖም ሞትን እንድንጋፈጥ ብቻችንን ትተውናል” ሲሉም ነው ፕሬዝዳንቱ በትናንቱ የቪዲዮ መልዕክታቸው የተናገሩት።