ፑቲን የዩክሬን ጦርነትን በፍጠነት የመቋጨት ፍላጎት እንዳላቸው የቱርኩ ፕሬዝዳንት ገለጹ
ፕሬዝዳት ኤርዶጋን አሁን ላይ ነገሮች ለሩሲያ በጣም አስቸጋሪ መሆናቸውን ጠቁመዋል
ሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በቅርቡ የ200 እስረኞች ልውውጥ እንደሚኖር ጠቁመዋል
የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይብ ኤርዶጋን፤ የሩሲያው ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬንን ጦርነት ለመቋጨት እንደሚፈልጉ አስታወቁ።
ይህም የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ከሰባት ወራት ወዲህ ትልቅ እርምጃ እንደሚሆን ተናግረዋል።
የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይብ ኤርዶጋን እና የሩሲያው ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን በቅርቡ በኡዝቤኪስታን ተገናኝተው ተወያይተው ነበረ።
ውይይቱን አስመልክተው ፕሬዝዳት ኤርዶጋን ከአሜሪካ ፒ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ጣያ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ፕሬዝዳንት ፑቲን ይህንን ጦርነት በተቻላቸው ፍጥነት ለመቋጨት ይፈልጋሉ ብለዋል።
የዩክሬን ጦር በያዝነው ወር በጀመረው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በሩሲያ እጅ ያሉ አካባቢዎችን ማስለቀቅ ጀምሯል።
ፕሬዝዳት ኤርዶጋን አሁን ላይ ነገሮች ለሩሲያ በጣም አስቸጋሪ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በቅርቡ የ200 እስረኞች ልውውጥ እንደሚኖርም ፕሬዝዳት ኤርዶጋን አስታውቀዋል።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ሰባት ወራት ሊሞላው ጥቂት ቀናት የሚቀሩት ሲሆን በጦርነቱ ከ10 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን ወደ ጎረቤት ሀገራት ሲሰደዱ ለዘመናት የተገነቡ መሰረተ ልማቶችም እየወደሙ ይገኛሉ።