አስር የቀድሞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ
ፖሊስ የሚፈልጋቸው አስሩ ግለሰቦች ከሕወሓት ተልዕኮ በመቀበል ሲሰሩ እንደነበር ተገልጿል
የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው በሀገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው ተብሏል
ተጠርጣሪዎቹ መንግስት እና ህዝብ የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ወደ ጐን በመተው “መቀመጫቸውን ትግራይ ክልል ካደረጉ ፀረ-ሠላም ከሆኑ የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል“ የሚሰሩ እንደነበሩ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ከሕወሓት ሀይሎች ተልዕኮ በመቀበል “ሀገር የመበተን፣ ሁከትና ብጥብጥ የመፍጠር እና ህገ-መንግስታዊ ሥርአቱን አደጋ ላይ የመጣል ተግባር ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ መንገድ በመሳተፍ ህዝብ በመንግስት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው በማድረግ የሀገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል“ እንደተጠረጠሩም የፖሊስ መረጃ ያመለክታል፡፡
የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው ፣ በተለያየ የአመራር ደረጃ ላይ የነበሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች የሚከተሉት ናቸው፡-
1) ኮማንደር ሰለሞን አብርሃ ብስራት
2) ኮማንደር ሀይለማርያም ብርሃኔ ገ/ማርያም
3) ም/ኢ/ር ክብሮም ገብሩ ገ/እግዚአብሄር
4) ም/ኢ/ር አረጋዊ ገ/ሂወት አስፋዉ
5) ረ/ኢንስፔክተር ገዛኢ ገ/ሂወት ገ/ስላሴ
6) ረ/ኢንስፔክተር ተስፋ ኪሮስ ግደይ
7) ረ/ኢንስፔክተር አርአያ ገ/አናንያ ኪዳኑ
8)ረ/ኢንስፔክተር ሰለሞን ወላይ ወ/አብዝጊ
9) ዋ/ሳጅን ሀይላይ ወልዱ ገ/ማርያም
10) ዋ/ሳጅን ሀፍቱ ካህሳይ አብርሃ
የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው ግለሰቦች አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ተግባር የተለያዩ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገጹ ጥሪ አቅርቧል፡፡