አውስትራሊያ ከ 800 በላይ ሩሲያውያን ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል
የአውስትራሊያ መንግስት የሩሲያ ወርቅ ወደ ግዛቱ እንዳይገባ እገዳ መጣሉን አስታወቀ፡፡
አውስትራሊያ የሩሲያን ወርቅ ከማገዷም በላይ ለዩክሬን ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ በዩክሬን ጉብኝት አድርገው ከተመለሱ በኋ ለኪቭ ድጋፍ እንዲደረግ ወስነዋል ተብሏል፡፡
በዚህም መሰረት አውስትራሊያ 34 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ወደ ዩክሬን እንድላኩ ወስናለች፡፡ የጠቅላይ ሚኒሰትር አንቶኒ አልባኔዝ አስተዳደር በሩሲያ ባለስልጣናትና ባለሀብቶች ላይ ተደጋጋሚ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል፡፡
እስካሁን 843 ሩሲያውያን እስካሁን በአውስትራሊያ ማዕቀብ እንደተጣለባቸው ተገልጿል፡፡ አውስትራሊያ በሩሲያውያኑ ላይ የጉዞ እገዳ ጭምርም ማስቀመጧ ነው ይፋ የተደረገው፡፡
አውስትራሊያድሮንን ጨምሮ ሌሎች ዋጋቸው 68 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ቁሳቁሶችን ለዩክሬን ለመስጠት መወሰኗ በተደጋጋሚ ተገልጿል፡፡ አውስትራሊያ በድምሩ 390 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ ለዩክሬን እንደምትሰጥ ገልጻለች፡፡
የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር በኪቭ ግዛት ውስጥ በጦርነት የተጎዱትን አልባኒዝ ቡቻ፣ ኢርፒን እና ሆስቶሜል የሚባሉትን ከተሞች መጎብኘታቸው ተገልጿል፡፡
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በቅርቡ በሰጠው መግለጫ ፤ ዩክሬን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በአውሮፓ ውስጥ ታይቶ የማያውቅ 'ጭካኔ' እያጋጠማት ነው ብሎ ነበር።