ፈረንሳዊው ግለሰብ በ48 አመት ውስጥ 9 ቶን ብረት እንደተመገበ ይገመታል
ፈረንሳውያን ሚሸል ሎቲቶን “ምስዩ ማዡቱ” ወይም “ሁሉን በሊታው” እያሉ ይጠሩታል።
ሎቲቶ በዘጠኝ አመቱ የጀመረው ብረት የመብላት ልማድ እስከ 57 አመቱ ድረስ ዘልቋል።
የትኛውንም አይነት ብረት እንዲመቸው አድርጎ ከቆረጠ በኋላ እንደ መድሃኒት ይውጠዋል፤ እንዲዋሃደለትም ውሃ በደንብ ይጠጣል።
በየቀኑ 900 ግራም ብረት የሚመገበው ይህ ፈረንሳዊ፥ በሁለት አመት ውስጥ አውሮፕላን ቀረጣጥፎ በመብላትም ስሙ ከፈረንሳይ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ናኝቷል።
18 ብስክሌቶች፣ 15 የሱፐርማርኬት እቃ ማመላለሻ ጋሪዎች፣ ምላጭ፣ የብረት ቁርጥራጮች በአጠቃላይ የማይፈጭ የሚመስሉን ነገሮችን ሁሉ በልቷል።
አስገራሚው ነገር ሎቲቶ በፈረንጆቹ 2007 ህይወቱ ያለፈው ብረት በመመገቡ ጤናው ታውኮ ሳይሆን በሌላ ህመም ነው ይላል ድንቃድንቅ ጉዳዮችን የሚመዘግበው ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ።
ፈረንሳዊው የብረት ቀበኛ በ48 አመት ውስጥ 9 ቶን ብረት እንደተመገበ ይገመታል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic