ፍርድ ቤቱ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የሚቀርቡ ምስክሮች ስም ዝርዝር እንዲገለፅ ወሰነ
ዐቃቤ ሕግ የምስክሮቹን ስም ዝርዝር ለዳኞች፣ ለጠበቆች እና ለተከሳሾች ብቻ ሰጥቶ ነበር
ውሳኔውን ተከትሎ በከሳሽ ዐቃቤ ህግ የቀረቡ የ9 ምስክሮች ስም ዝርዝር ይፋ ሆኗል
ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የሚያቀርባቸው ምስክሮች ስም ዝርዝር በመገናኛ ብዙሃን እንዲገለፅ ተወሰነ፡፡
ምስክሮቹ ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በግልፅ ችሎት እንዲመሰክሩ ተወስኗል፡፡
ይህ የተወሰነው የእነ እስክንድር ነጋን የዛሬ የጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም የክስ ቀጠሮ በተመለከተው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው፡፡
ባልደራስ እነ እስክንድር ነጋ ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲለቀቁ ጠየቀ
ችሎቱ ዐቃቤ ሕግ በግልፅ ችሎት እንዲያቀርባቸው የታቀዱ ምስክሮች ስም ዝርዝር ለመገናኛ ብዙሃን እንዳይገለጽ ያቀረበውን የጽሁፍ አቤቱታ ውድቅ አድርጓል፡፡
በዐቃቤ ህግ ምስክርነት በግልጽ ችሎት የሚቀርቡ ዘጠኝ ምስክሮች ስም ዝርዝር ለመገናኛ ብዙሃን እንዲገለጽም ወስኗል፡፡ ውሳኔውን ተከትሎም የምስክሮቹ ስም ዝርዝር ይፋ ሆኗል፡፡
ዐቃቤ ሕግ የዘጠኝ ምስክሮችን ስም ዝርዝር ለዳኞች፣ ለጠበቆች እና ለተከሳሾች ብቻ ሰጥቶ ነበር፡፡ የምስክሮቹ ስም አይገለጽ መባሉን የተቃወመው እስክንድር ነጋ ምስክሮች እንዲፈሩ ሳይሆን ህዝብ እውነታውን ሊረዳ እንደሚገባ በማስታወቅ ስም ዝርዝራቸው እንዲገለጽ ጠይቋል፡፡
ዐቃቤ ህግ በአጠቃላይ 19 ምስክሮችን ነው ያቀረበው፡፡ ምስክሮቹ ከመጋረጃ ጀርባ ይመስክሩ በሚል ያቀረበው ጥያቄ ሲያከራክር መቆየቱ ይታወሳል፡፡
እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ከሰኔ 22ቱ (2012 ዓ/ም) የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ግጭት እንዲቀሰቀስ አድርጋችኋል በሚል ነው የታሰሩት፡፡
እነ አቶ እስክንድር ነጋ የምርጫ ዕጩ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰርተፍኬት ሊሰጣቸው ነው
በቅርቡ ከሌሎች የፖለቲካ አጋሮቹ ጋር በመሆን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የተሰኘ ክልላዊ ፓርቲ መስርቶ ወደ ፖለቲካው የገባው ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ከ10 የሚልቁ ዓመታትን በእስር ማሳለፉ ይታወሳል፡፡
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አቶ እስክንድር ነጋን እና ሌሎች የፓርቲው አመራሮችን ከእስር የማስፈታት ግፊት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ንን ጨምሮ፣ ለ15 አገራት ኤምባሲዎች ጥሪ ማቅረቡን ማስታወቁም አይዘነጋም፡፡