ሰሜን ዕዝ ሲጠቃ ግዴታቸውን ያልተወጡ 178 የትግራይ ተወላጅ ወታደሮች በይቅርታ ከእስር መፈታታቸውን ሰራዊቱ አስታወቀ
ሰራዊቱ እንደገጸለው ወታደሮች በወታደራዊ ፍርድ ቤት ተከሰው ጥፋተኛ ተብለው እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣት ተላልፎባቸው የነበሩ ናቸው
ወታደሮቹ የተፈቱት በፈጸሙት ወንጀል ተጸጽተው ለመንግስት የይቅርታ ቦርድ እና ለመከላከያ ሚኒስቴር የይቅርታ ጥያቄ በማቅረባቸው ነው ብሏል ሰራዊቱ
ግዴታቸውን ባለመወጣት ተከሰው ጥፋተኛ የተባሉ ወታደሮች በይቅርታ ከእስር መፈታታቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊት አስታወቀ።
መከላከያ ሰራዊት በሬስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል ሰፍሮ የነበረው ሰሜን ዕዝ በተጠቃበት ወቅት ግዴታቸውን ባለመወጣት ጥፋተኛ የተባሉ 178 የትግራይ ተወላጅ የሰራዊቱ አባላት የሆኑ ወታደሮች በይቅርታ ከእስር መፈታታቸውን አስታውቋል።
ሰራዊቱ የህወሓት ታጣቂዎች ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም "በክህደት መንፈስ" በዕዙ ላይ ጥቃት በከፈቱበት ወቅት እነዚህ የሰራዊት አባላት "የተሰጣቸውን ህገመንግስታዊ ተልእኮ ወደ ጎን በመተው በሰራዊቱ እና በህዝብ ጥቅሞች" ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ብሏል።
ሰራዊቱ እንደገጸለው ወታደሮቹ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ተከሰው ጥፋተኛ ተብለው እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣት ተላልፎባቸው የነበሩ ናቸው።
ወታደሮቹ የተፈቱት በፈጸሙት ወንጀል ተጸጽተው ለመንግስት የይቅርታ ቦርድ እና ለመከላከያ ሚኒስቴር የይቅርታ ጥያቄ በማቅረባቸው ነው ብሏል ሰራዊቱ።
በሰሜን ኢትዮጵያ በህወሓት እና በፌደራል መንግስት መከላከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ባለፈው አመት ህዳር ወር በፕሪቶሪያ በተፈረመው የዘላቂ ሰላም ስምምነት መቆሙ ይታወሳል።
የወታደሮቹ የይቅርታ ጥያቄ ለይቅርታ ቦርድ ቀርቦ ተቀባይነት ማግኘቱን መከላከያ ሰራዊት ገልሏል።
ሰራዊቱ አክሎም መከላከያ ሚኒስቴር የይቅርታ ቦርዱን ውሳኔ መሰረት አድርጎ ታሰረው ከነበሩት የትግራይ ተወላጅ ወታደሮች ውስጥ 178ቱ እንዲፈቱ ከዛሬ ጀምሮ እንዲፈቱ ወስኗል ብሏል።