ዲ. አር ኮንጎ የግድቡ የሶስትዮሽ ድርድር በቶሎ እንዲጀመር እያግባባች ነው
ኢትዮጵያ ወደ ድርድሩ ለመመለስ ያላትን ቁርጠኝት ትናንት ለልዑኩ መግለጿ የሚታወስ ነው
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የተመራ ልዑክ በተደራዳሪ ሃገራቱ ጉብኝት በማድረግ ላይ ነው
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መካከል የሚደረገው አፍሪካ ህብረት መር የሶስትዮሽ ድርድር በቶሎ እንዲጀመር እያግባባች ነው፡፡
በዲ. አር ኮንጎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፊ ሉቱንዱላ የተመራ ልዑክ በተደራዳሪ ሃገራቱ ጉብኝት ማድረግ ጀምሯል፡፡
ጉብኝቱ ሃገራቱ አቋርጠው ወደ ቆዩት ድርድር በቶሎ እንዲመለሱ ለማግባባት የሚደረግ ነው፡፡
የመጀመሪያ ጉብኝቱን በኢትዮጵያ ያደረገው ልዑኩ ትናንት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይቷል፡፡
የህዳሴ ግድብ የጀነሬተር አንቀሳቃሽ አካል የማስቀመጥ ሥራ ተከናወነ
ውይይቱ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢ/ር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) እንዲሁም የግድቡ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ኮሚቴ አባል ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው ተገኝተዋል፡፡
አቶ ደመቀ በውይይቱ ኢትዮጵያ አፍሪካ ህብረት መር ወደሆነው የሶስትዮሽ ድርድር ለመመለስ ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡
ዲ.አር ኮንጎ ላደረገችው ያላሰለሰ ጥረት አመስግነዋልም ነው አቶ ደመቀ፡፡
ልዑኩ የአዲስ አበባ ቆይታውን አጠናቆ ትናንት ካርቱም የገባ ሲሆን ከሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መርየም አል ሳዲቅ አል ማህዲ ጋር ተወያይቷል፡፡
የግድቡን 2ኛ ዙር ሙሌት ለማደናቀፍ በ37 ሺህ ኮምፒውተሮች ላይ ተነጣጥሮ የነበረ የሳይበር ጥቃት ማከሸፍ ተችሏል
መርየም የዲ. አር ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሼስኬዲ እና አፍሪካ ህብረት በግድቡ ጉዳይ መፍትሔ ለማበጀት ለሚያደርጉት ጥረት ማመስገናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ልዑኩ ከደቂቃዎች በፊት ግብጽ ደርሶም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
ውይይቱ ሊቀጥል ስለሚችልበት ጉዳይ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡
ሶስቱ ሃገራት በፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሼስኬዲ አግባቢነት በኪንሻሳ ሲያደርጉት የነበረው ውይይት ያለ ስምምነት መጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡
ውይይቱ ከዚያም ወዲህ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡