ቤኒሻንጉል አዲስ ክልላዊ የፀጥታ ስትራቴጂ ሊነደፍ እንደሚገባ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ
በተመሳሳይ ወቅት በሌሎች የክልሉ ወረዳዎች የተሰነዘሩ ጥቃቶች በመኖራቸው የተጎጂዎቹ ቁጥር ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችልም ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው
በክልሉ በድባጤ ወረዳ በመንገደኞች ላይ በተፈጸመው ዘግናኝ ጥቃት የተጎዱ ሰዎች ቁጥር 34 መድረሱን ኮሚሽኑ አስታውቋል
ቤኒሻንጉል አዲስ ክልላዊ የፀጥታ ስትራቴጂ ሊነደፍ እንደሚገባ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ፋታ የማይሰጥ ሆኖ መቀጠሉን አስታወቀ፡፡
ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ በፌዴራሉ እና በክልሉ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መካከል ፍጥነትና ንቁ ሆኖ መጠበቅ ላይ የተመሰረተ የተሻለ ቅንጅትን የሚሻ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከሰሞኑ በክልሉ በድባጤ ወረዳ ከወንበራ ወደ ቻግኒ በመጓዝ ላይ በነበረ የሕዝብ ማመላሻ አውቶብስ ላይ በተፈጸመው ዘግናኝ ጥቃት የተሰማውን ኃዘንም ገልጿል።
በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር 34 መድረሱን ደረሰኝ መረጃ መሰረት ማረጋገጡንም ነው ያስታወቀው፡፡
ሆኖም በተመሳሳይ ወቅት በሌሎች የክልሉ ወረዳዎች (ውብጊሽ፣ያምፕ እና ቂዶህ) ጥቃት በመሰንዘሩ እና ለጊዜው ሕይወታቸውን ለማዳን የሸሹ ሰዎች መኖራቸው በመነገሩ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ይጠበቃል እንደ ኮሚሽኑ ገለጻ፡፡
የፌዴራሉ እና የክልሉ የፀጥታ አካላት ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ሊቀናጁ ይገባል ያሉት ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል “እነዚህን ጥቃቶች ሊያስቆም የሚችል አዲስ ክልላዊ የፀጥታ ስትራቴጂ ሊነድፉ ይገባል” ሲሉ ስለመናገራቸው ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡