ጦር መሳሪያው በህብረተሰቡ ጥቆማ በግለሰብ ቤት ተከማችቶ የተገኘ ነው ተብሏል
“የኤርትራ ተቃዋሚዎች ይጠቀሙበት ነበር” የተባለለት በርካታ ጦር መሳሪያ በሁመራ ተያዘ
በሁመራ ከተማ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎች በግለሰብ ቤት ተከዝኖ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ፡፡
ጦር መሳሪያዎቹ በምዕራብ ግንባር ህግን ለማስከበር እየተወሰደ ባለው እርምጃ በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው ያሉት የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው “ጦር መሳሪያው ትህነግ የኤርትራና የኢትዮጵያ መንግስትን ለመቃወም ያሰለጠናቸው ቡድኖች ይጠቀሙበት የነበረ ነው” ብለዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ ከአማራ ልዩ ሀይል ጋር በመሆን ባደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት ኦፕሬሽን የጦር መሳሪያዎቹ ሊያዙ እንደቻሉም ተናግረዋል ዋና አስተዳዳሪው።
ከተያዙ መሳሪያዎች መካከል
የክላሽ መትረይስ 9፣
ኤፍኤን 26፣
ጂ ኤም3 27፣
ክላሽ 65፣
የክላሽ ካዝና 139፣
የጂኤም3 ካዝና 17፣
የወገብ ትጥቅ 12፣
የዲሽቃ ሽንሽን ከ99 ጥይት ጋር 1፣
የጦር መነፀር 7፣
መገናኛ ሃይኮም 2፣
አገልግል ካዝና 20፣
የመገናኛ ስታንድ 1፣
አርቢጂ /ላዉንቸር/ 2፣
የብሬን ተቀያሪ አፈሙዝ 11፣ እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡
መሳሪያዎቹ ለዞኑ ሚሊሻ ገቢ ፅ/ቤት መደረጋቸውንም ነው ዋና አስተዳዳሪ ያስታወቁት
ዘገባው የዞኑ ኮሙኒኬሽን ነው፡፡