ኢሰመኮ በምዕራብ ወለጋ በሲቪል ሰዎች ላይ "ከፍተኛ ጉዳት" መድረሱን ገለጸ
ግድያው የተፈጸመው በመንግሰት እና በሸኔ ታጣቂ ቡድን መካከል ከነበረውን ውጊያ ጋር ይያያዛል ብሏል
ኢሰመኮ አሁንም በአባቢው የጸጥታ ስጋት በመኖሩ ነዋሪዎቹ ድጋፍ እየጠየቁ ነው ብሏል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮማሽን(ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በትናንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ በመግስት እና መንግስት በሽብር በፈረጀው የሸኔ ታጣቂ ቡድን መካከል ከነበረውን ውጊያ ጋር በተያያዘ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ብሏል።
ታጣቂ ቡድኑ በአካባቢው በሚኖሩ ሲቪል ሰዎች ላይ የህይወት፣ የአካል እና የንብረት ጉዳት ማድረሱን የገለጸው ኢሰመኮ የጸጥታ ሰጋት በመኖሩ ነዋሪዎቹ አሁንም ድጋፍ እየጠየቁ ነው ብሏል።
ኢሰመኮ በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል አሮሞ ብሄረሰብ ዞን የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች የኦነግ ሸኔ አባላት ናቸው በተባሉ ሰዎች ላይ ከህግ ውጭ የሆነ ግድያ ፈጽመዋል ብሏል።
ይህን ከህግ ውጭ የሆነ ግድያ መጋቢት 2፣2014 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርቱ ማካተቱን የገለጸው ኢሰመኮ ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲሰፍን አሳስቧል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤ በቀለ"መንግሥት በሲቪል ሰዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈጸም አስፈላጊ የሆኑ የመከላከል እርምጃዎችን እንዲወስድ"እና ሐችግሩ ዘለቂ መፍትሄ ኦንዲሰጥ አሳስበዋል።
ኢሰመኮ በተለያዩ አካባቢዎች በመንግስት እና በታጠቁ ኃይሎች በሲቪል ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለዉን ጥቃት እየተከታተልኩት ነው ብሏል።