የተመድ እና ኢሰመኮ ምርመራ ቡድን በትግራይ ያካሄዱትን የመስክ ስራ ማጠናቀቃቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ
ሁለቱ ተቋማት በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል በተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ በጋራ ሲመረምሩ ቆይተው ነበር
ተቋማቱ የጋራ ምርመራቸውን ያካሄዱት ከፈረንጆቹ ግንቦት 16 አስከ ነሀሴ 20 ቀን 2021 ድረስ ሲሆን ከ200 በላይ ሰዎችን ቃለመጠይቅ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል
የህወሃት ሀይሎች፣ በትግራይ ክልል በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ በፈጸሙት ጥቃት ምክንያት ነበር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጀመረው።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) እና የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ ፣ ከትግራይ ግጭት ጋር በተያያዘ ተፈጽመዋል በተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች ላይ የጋራ ምርመራ ከወራት በፊት ተስማምተው ነበር፡፡
- ኢሰመኮ በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ጉዳቶችን የሚመረምር የባለሞያዎች ቡድን ሊያሰማራ ነው
- የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የትግራይ እና አማራ ክልሎችን እንደሚጎበኙ ገለጹ
በርካታ ሀገራት እና የሰብዓዊ መብት ተቋማት በትግራክ ክልል ሴቶች ተደፍረዋል፤ንጹሀን በጅምላ ተገድለዋል፤ ረሀብ ለጦርነት እንዲውል ተደርጓል እና መሰል የሰብዓዊ መበት ጥሰቶች ተፈጽመዋል የሚሉ ሀሳቦች ሲወጡ ነበር።
እነዚሁ ተቋማት እና ሀገራት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የአርትራ ጦር ጥቃቱን እንደፈጸሙ ክስ ሲያቀርቡ ነበር።
የኢትዮጵያ መንግስት እና የኤርትራ ጦር ክሱን አስተባብለው ምርመራ እንዲካሄድ በተደረሰው ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጋራ ምርመራ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ዋና መቀመጫውን ጀኔቫ፣ ስዊዘርላንድ ያደረገው የተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት መሰረት ሁለቱ ተቋማት የመስክ ምልከታ አድርገው መረጃዎችን፤ቃለመጠይቆችን እና ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ ስራዎችን እንዳጠናቀቁ ገልጿል።
የመስክ ምርመራ ስራው የተካሄደው በመቀሌ፤ውቅሮ፤ሳምረ፤አላማጣ፤ቦራ፤ማይጨው፤ዳንሻ፤ማይካድራ፤ሁመራ፤ ጎንደር ፤ባህርዳር እና አዲስ አበባ ከተሞች በመሄድ ምርመራ ማካሄዳቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።
ተቋማቱ የጋራ ምርመራቸውን ያካሄዱት ከፈረንጆቹ ግንቦት 16 አስከ ነሀሴ 20 ቀን 2021 ድረስ ሲሆን ከ200 በላይ ሰዎችን ቃለመጠይቅ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።
በሁለቱ የጋራ ተቋማት የመስክ መርማሪዎች በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን፤ የአይን ምሰክሮች፤የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ሰራተኞችን፤ የክልል እና የፌደራል ተቃማት ሰራተኞችን እና አመራሮችን፤ የህክምና ባለሙያዎችን፤የፍትህ አካላትን፤ እና ሌሎች ስለ ጉዳዩ ያውቃሉ የተባሉ አካላትን እና ተቋማትን ሁሉ ቃለመጠይቅ ማድረጋቸው ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም የምስል እና የዶክመንት ማስረጃዎችን፤ ቪዲዮዎችን እና ሌሎች ለምርመራ ይጠቅማሉ የተባሉ መረጃዎችን ሁሉ ማሰባሰባቸውንም ተቋማቱ ጠቅሷል።
ይሁንና በአካባቢዎቹ የደህንነት ችግር መኖሩለምርመራ ስራው እንቅፋት እንደሆነባቸው ተገልጿል።ሁሉ የጋራ የሰብዓዊ መብት ተቋማት የተጠቃለለ የምርመራ ሪፖርታቸውን የፊታችን በፈረንጆቹ ህዳር 1 ቀን 2021 ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።