የፌደራል መንግስት ከህወሓት ከባድ መሳሪያ መረከብ መጀመሩን ገለጸ
በርክክቡ ስነ ስርአት ላይ የአፍሪካ ህብረት ታዛቦዎች መገኘታቸውን በከላከያ ሰራዊት ገልጿል
የስምምነቱን ትግበራ የሚካታተለው ቡድንም የህወሓት ትጥቅ መፍታት እና የፌደራል መንግስት ያልሆኑ ኃይሎች ከትግራይ መውጣት መጀመሩን አስታውቋል
የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሓት ከባድ የጦር መሳሪያዎች መረከብ መጀመሩን መጀመሩን መከላከያ ሰራዊት አስታውቃል፡፡
የሁለቱን አመት ግጭት ይፈታል በተባለው የደቡብ አፍሪካው የፌደራል መንግስት እና የህወሓት ስምምነት፤ የህወሓት ተዋጊዎች ትጥቅ ፈትተው ለመንግስት እንዲያስረክቡ ያስገድዷል፡፡
በስምምነት መሰረት መንግስት ህወሓት ታጥቆት የነበረው ከባድ መሳሪያ መረከብ መጀመሩን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡
መከላከያ ስራዊት፤ የጦር መሳሪያ እርክክቡ እየተካሄደ ያለው ከመቀሌ በ36 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው አጉላ ካምፕ ነው ብሏል፡፡
የመከላከያ ሰራዊት አመራር የሆኑት ሌተናል ኮሎኔል አለሜ ታደለ መከላከያ ከባድ መሳሪያዎች ከህወሓት መረከቡን ገልጸዋል፡፡
መከላከያ ተረክቢለሁ ካላቸው የህወሓት ከባድ መሳሪያዎች መካከል ብረት ለበስ ታንኮች፤ የተለያዩ ሚሊ ሜትር መድፎች፤ሮኬቶች፤ ዙዎች፤ ሞርተሮች ይገኙበታል፡፡
በርክክቡ ስነ ስርአት ላይ የአፍሪካ ህብረት ታዛቦዎች መገኘታቸውን በከላከያ ሰራዊት ገልጿል፡፡
የስምምነቱን ትግበራ የሚካታተለው ቡድንም የህወሓት ትጥቅ መፍታት እና የፌደራል መንግስት ያልሆኑ ኃይሎች ከትግራይ መውጣት መጀመሩን አስታውቋል፡፡