በሀገር ክህደት ወንጀል ተጠርጥረው በተያዙ የጦር መኮንኖች ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው ተባለ
ከ300 በሚልቁ ከፍተኛ አመራሮችና የጦር መኮንኖች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ የሚታወስ ነው
ምርመራው በቁጥጥር ስር በዋሉ 15 የጦር መኮንኖች ላይ ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው
በተለያዩ ጊዜያት በሀገር ክህደት ወንጀል ተጠርጥረው የመያዣ ትዕዛዝ በወጣባቸዉ እና በተያዙ አመራሮችና የጦር መኮንኖች ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ የመያዣ ትዕዛዝ ቢወጣባቸውም ተደብቀዋል ያላቸውን አመራሮችና የጦር መኮንኖችን በማደን ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ/ም ትግራይ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከፈጸመው የህወሃት ቡድን ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመሳተፍ የጥፋት ስራው አካል ናቸው ብሎ በጠረጠራቸው ከ3 መቶ በላይ ከፍተኛ አመራሮችና የጦር መኮንኖች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ከፍርድ ቤት መውጣቱ ይታወቃል፡፡
ከነዚህም መካከል እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ እና የተደመሰሱ ከፍተኛ መኮንኖች አሉ፡፡ ምርመራው በመካሄድ ላይ ያለው በተያዙ 13 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ላይ ነው፡፡
ከከፍተኛ መኮንኖቹ መካከልም
1. ሜ/ጀኔራል ገ/መድህን ፈቃዱ ሀይሉ
2. ሜ/ጀኔራል ይዳው ገ/መድህን
3. ብ/ጀኔራል ገ/ህይወት ሲስኖስ ገብሩ
4. ብ/ጄኔራል ኢንሱ እጃጆ እራሾ
5. ብ/ጄኔራል ፍስሃ ገ/ስላሴ
6. ኮ/ል ደሳለኝ አበበ ተስፋዬ
7. ኮ/ል እያሱ ነጋሽ ተሰማ
8. ኮ/ል መብራቱ ተድላ ወ/ሚካኤል
9. ኮ/ል ባራኪ ጠማሎው ገብሩ
10. ኮ/ል ሀይላይ መዝገብ ማሾ
11. ኮ/ል ፍሰኃ ግደይ ወ/ማርያም
12. ሌ/ኮ/ል ሙዘይ ተሰማ ስዩም
13. ሌ/ኮ/ል ፍሰሃ በየነ ገ/ኪዳን
14. ሌ/ኮ/ል ምሩጽ ወ/አረጋይ ገ/መስቀል
15. ሌ/ኮ/ል ምሩጽ በርሄ አበራ ይገኙበታል፡፡
የሃገር መከላከያ ሰራዊት እና ፌዴራል ፖሊስ ባካሄዱት የህግ ማስከበር ዘመቻ እርምጃ የተወሰደባቸው 5 የጦር መኮንኖች አሉም ተብሏል፡፡
1. ኮ/ል ተስፋዬ ገ/መድህን
2. ኮ/ል የማነ ገ/ሚካኤል
3. ሌ/ኮ/ል ሀዲሽ ገ/ጻዲቅ
4. ኮ/ል ማዕሾ
5. ኮ/ል አለም ገ/መድህን ከነዚሁ እርምጃ ከተወሰደባቸው የጦር መኮንኖች መካከል ናቸው፡፡
ከጦር መኮንኖቹ በተጨማሪ በ81 የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ይታወሳል፡፡ አምባሳደር አዲስ ዓለም ባሌማ ከነዚሁ መካከል የቡድኑ አመራሮች መካከል አንዱ መሆናው እና በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወሳል፡፡
ኮሚሽኑ ያልተያዙ የቡድኑ እና የጦር አመራሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተለያዩ የኃይማኖት ተቋማት በየጥሻው እና በየዋሻው እያደነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ተፈላጊዎቹ በውጊያው ከተሸነፉ በኃላ ራሳቸውን ካለባበስ ጀምሮ በመቀያየር ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ እንዳሉ መረጃው ደርሶኛል ነው ያለው፡፡
ለዘመቻው ስኬት የትግራይን ህዝብ ያመሰገነ ሲሆን አሁንም አስፈላጊውን ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል፡፡