መንግስት "የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዕቅድ በተመለከተ ምክክር እየተደረገ ነው” አለ
"የትግራይ ታጣቂዎች" ጥትቅ የሚፈቱበት ዝርዝር ዕቅድ ላይ የሚሰራ የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽሬ ላይ እየመከረ ነው
የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት የ2 ዓመታትን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ከወር በፊት መፈራረማቸው አይዘነጋም
መንግስት "የትግራይ ታቂዎች" ሲል የጠራቸው ኃይሎች ትጥቅ የሚፈቱበትን "ዝርዝር ዕቅድ" የሚሠራ የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽሬ ላይ እየመከረ ነው ብሏል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ሕወሓት ትጥቅ የሚፈታበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚያዘጋጅ የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ከህዳር 21 ጀምሮ ስራውን ጀምሯል።
ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ታቂዎች የተውጣጣ የተባለው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ በሚቀጥሉት ቀናት ዝርዝር ዕቅድ በማውጣት ስራውን ያጠናቅቃል ተብሏል።
ኮሚቴው የሚያወጣው ዝርዝር ዕቅድ ትጥቅ የማስፈታት፣ ካምፕ የማስገባትና ተያያዥ ጉዳዮችን እንደሆነም መግለጫው ጠቅሷል።
በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት "የህውሃት ታጣቂዎች" ትጥቅ የሚፈቱበት ቀን የተቆረጠ ቢሆንም ገቢራዊነቱ ግን ዘግይቷል።
ከዚያም በናይሮቢ በተፈረመው ስምምነት "የውጭ ጦር" የተባለው የኤርትራ ጦር እንደሚወጣ ስምም ላይ መደረሱ የሚታወስ ነው።
እስካሁን የኤርትራ ጦር ለመውጣቱ ማረጋገጫ አልተሰጠም። የትግራይ መንግስት ሹማምንትም የኤርትራ ጦር ሲወጣ ብቻ ትጥቅ እንደሚፈቱ ተናግረዋል።
የትጥቅ መፍታት ዝርዝር ዕቅዱን የማውጣት ተግባሩ በቴክኒክ ጉዳዮች ምክንያት መዘግየቱንም የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።
የኢትዮጵያ መንግስትና ህውሃት የሁለት ዓመታትን ጦርነት በሰላም ለመፍታት መስማማታቸውን ተከትሎ እስካሁን ጦርነት በማቆም የሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ ተደርጓል።