“በሁሉም ግንባር ያለው የመከላከያ ሰራዊት ከነሙሉ ቁመናው ነው ያለው”- ዶ/ር ለገሰ ቱሉ
መንግስት፤ ሀገር ለማዳን የዘመተ መሪን “የኔቤል ተሸላሚ ሆኖ እንደት ዘመተ“ ማለት ትክክል አይደለም ብሏል
ህወሃት በርካታ የሰራዊት አባል “ማርኪለሁ” በሚል የሚያሰራጨው ምስል ውሸት መሆኑ ተገለጸ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አሁን ላይ ከነሙሉ ትጥቁና ከነሙሉ የሰው ኃይሉ እንደሆነ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አስታወቁ።
ሚኒስትሩ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብር ከሚፈልጋቸው የህወሃት አመራሮች አንዱ የሆኑት ክንዲያ ገ/ህይወት ከ11 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሰራዊት እንደማረኩ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። ይህንን የትዊተር ጹሑፍ ዋቢ በማድግ መገናኛ ብዙኃን የኢትዮጵያ ሰራዊት መማረኩንና መዳከሙን እየገለጹ ነው፡፡
ከአል ዐይን ኒውስ ጋር ቆይታ ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፤ ህወሃት በርካታ ወታደሮችን እንደማረከ አድርጎ የሚያሳየው ተንቀሰቃሽ ምስል የውሸት እንደሆነ ተናግረዋል።
ተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ በርካታ ወታደሮች እንደተማረኩ ተደርጎ የተቀረጸው ምስል ፊታቸውን እንደማያሳይና ፊታቸው በደንብ እንደማይታይ ገልጸዋል። ይህ የተደረገውም የውሸት ለማድረግ ነው ብለዋል።
አሁን ህወሃት በያዛቸው አካባቢዎች ወጣቶችን በመሰብሰብ በተለያየ መልክ “ለማጭበርበር ያስቀመጧቸው ዩኒፎርሞችን በማልበስ እነዚህ የተማረኩ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ናቸው ይላሉ” ሲሉም ሚኒስትሩ ምላሽ ሰጥተዋል።
የተማረኩ ጥቂት ወታደሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ያነሱት ዶ/ር ለገሰ፤ እነዚህን ከፊት በማድረግ “እንደዚህ ብላችሁ ተናገሩ” እንደሚሏቸው ገልጸዋል።
ህወሃት ተንቤን አካባቢ እያለ የተወሰነ የማረከው እንደሚኖር ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ከዛ ውጭ ግን ከሃይቅና ወረባቦ ውጊያ በኋላ አንኳን ሰው መሳሪም እንዳልማረኩ ተናግረዋል።
በተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚታየው ይህንን ያህል ሰራዊት ከማረኩ መሳሪያ አገኙ ማለት ነው ያሉት ዶ/ር ለገሰ ህወሃቶች ምንም አይነት ነገር እንዳላገኙና በተንቀሰቃሽ ምስል የቀረበው የተቀናበረ ውሸት መሆኑንም ለአል ዐይን አማርኛ አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ “በዚህ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ሰው ሁለት ሰው አይኖርም ባይባልም እንደዚህ እንደሚባለው አይነት ነገር የለም” ሲሉም ነው ምላሽ የሰጡት።
ህወሃት “መከላከያ ሰራዊት የለም ብዙ ማርከናል ካለ ሰራዊቱ የታጠቀውን ዘመናዊ መሳሪያ መታጠቅ ይችል ነበር፤ አሁን የመሳሪያ አቅማቸው ደካማ ነው፤ የላቸውም ተመቶባቸዋል” ብለዋል፡፡
በሁሉም ግንባር ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከነሙሉ የሰው ኃይሉ፤ ከነሙሉ ትጥቁ፤ እንደሆነም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ኪሳራውን እንኳን ከተወሰደ ከመንግስት አንድ ከተባለ ከህወሃት 30 ኪሳራ እንደሚኖርም ገልጸዋል።
የውጭ መገናኛ ብዙኃን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደግንባር መሄድ አስመልክቶ “እንደት የኔቤል ተሸላሚ ሆኖ “ እያሉ “የሚያናፍሱ” እንዳሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የቀድሞው አሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ኖቤል ተሸላሚ ሆነው የሀገራቸው ጦር በሊቢያና በሌሎች ሀገሮች ላይ ጣልቃ ገብተው ምንም ባልተባሉበት ሁኔታ ሀገራቸውን ለማዳን መዝመታቸው “እንደት የኔቤል ተሸላሚ ሆኖ “ የሚስብል እንዳልሆነ ገልጸዋል።