የጊኒ ጁንታ መሪ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት በመሆንበመሆን ቃለ መሃላ ፈፀሙ
የ41 ዓመቱ ኮሎኔል ማማዲ ዱምቦያ በአፍሪካ ሁለተኛው በእድሜ ትንሹ መሪ መኆን ችለዋል
ማማዲ ዶምቦያ ፡ የቀድሞው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴን “ደህና ናቸው” ከማለት ውጭ ያሉበት ቦታ የት እንደሆነ ከመናገር ተቆጥቧል
የጊኒን መፈንቅለ መንግስት በመምራት በትረ-ስልጣን የጨበጡት ኮሎኔል ማማዲ ዱምቦያ የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መኃላ ፈጸሙ።
ቃለ መኃላ የፈጸሙት ኮሎኔል ማማዲ ዶምቦያ በቀጣይ ሳምንት ሲቪል አስተዳደር ያዋቅራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አዲሱ ፕሬዝዳንት ቃለ መኃላ በፈጸሙበት ወቅት አዲስ ህገ-መንግስት በማርቀቅ ጊኒን እንደ አዲስ ለማዋቀር እንደሚሰሩ፣ ሙስናን እንደሚታገሉ እንዲሁም ግልጽና ተዓማኒ ምርጫ እንደሚያካሂዱ መናገራቸውን ኣጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ ግልጽና ተዓማኒ ምርጫ እንዲካሄድ ደርጋለሁ ብለው ቃል ቢገቡም ምርጫው መች ይካሄዳል ለሚለው እስካሁን በግልጽ ያሉት ነገር የለም።
ጊኒ በቀጠናውም ሆነ በአህጉሪቱ ስታከናውናቸው የነበሩ ተግባራትና ግዴታዎች ለማስቀጠልም አዲሱ ፕሬዝዳንት ቃል ገብተዋል።
የጊኒ መፈንቅለ መንግስት መሪ ኮሎኔል ማማዲ ደንቦያ የፈረንሳይ ጦር አባል ነበር ተባለ
የ41 ዓመቱ ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ፤ በማሊ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኬይታን ከስልጣን በማስወገድ በትረ ስልጣን ከተረከቡት የ38 ዓመቱ ኮሮኔል ኣሲሚ ጎይታ ቀጥሎ በአፍሪካ ሁለተኛው በእድሜ ትንሹ መሪ መሆንም ችለዋል።
አዲሱ ፕሬዝዳንት ማማዲ ዶምቦያ ፡ በመፈንቅለ መንግስት ያስወገድዋቸው የ83 ዓመት አዛውንቱ የቀድሞው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴን በተመለከተ “ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ” ላይ ይገኛሉ ከማለት በዘለለ ያሉበት ቦታ የት እንደሆነ ከመናገር ተቆጥበዋል።
ኮሎኔል ማማዲ ዶምብያ፡ መፈንቅለ መንግስት ከመምራታቸው በፊት ብዙ የሚታወቁ ወታደራዊ መኮንን ባይሆኑም፤ ባላቸው ዓለም አቀፍ ወታደራዊ ልምድ መፈንቅለ መንግስቱን ሊያሳኩ እንደቻሉ የምዕራብ አፍሪካ የፖለቲካ ተንታኙ ፖል መሊ ተናግሯል።
“በጊኒ መፈንቅለ መንግስት ከማድረግ ውጭ ምንም አማራጭ አልነበረም”፡-የጊኒ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲያሎ
ኮሎኔል ማማዲ ዶምብያ፡ በፈረንሳይ ወታደራዊ ትምህርት መውሰዳቸውን ተከትሎ በፈረንሳይ ወታደር ቤት ማገልገል የቻሉ ናቸው።
ከዘህም በተጨማሪ ኮሎኔሉ በ15 ዓመት የወታደር ቤት ቆይታቸው በአፍጋኒስታን፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጁቡቲ፣ ማእከላዊ ሪፓብሊክ አፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት በተልዕኮ አገልግለዋል።