“ሆስፒታሎች በግጭት ምክንያት የቆሰሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታካሚዎችን እያስተናገዱ ነው” የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ
የግጭት ተዋናይ ሆኑ ኃይሎች ንጹሀን፣ የህክምና ቁሳቁሶች እና ባለሙያወች ድህንነት እንዲጠብቁ ኮሚቴው ጠይቀዋል
የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመሆን ለሆስፒታሎች መሰረታዊ ድጋፍ እያደረኩ ነውም ብሏል
የግጭት ተዋናይ የሆኑ ኃይሎች ንጹሀን ዜጎችን፣ የህክምና ማእከላትን እና ባለሙያዎችን እንዲጠብቁ የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጥሪ አቀረበ።
ኮሚቴው ይህንን ያለው አሁን ላይ በሀገሪቱ የሚገኙ ሆስፒታሎች በግጭቱ ምክንያት የቆሰሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታካሚዎች በማስተናገድ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ነው።
በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች የተከሰተው ግጭት ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን የገለጸው ኮሚቴው፤ በግጭቱ ምክንያት የተጎዱ ዜጎችን ለመታደግ የህይወት አድን የህክማና ድጋፍ የመስጠቱ ተግባር በማሳደግ ለይ መሆኑንም ገልጿል።
በተለያዩ ክልሎች ያለውን ፍላጎት ለማሟላት ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተበበር እየሰራ መሆኑንም የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል።
በዚህም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሆስፒታሎችና ጤና ተቋማት የሚደረገው የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ እያደገ መምጣቱን ኮሚቴው ገልጿል።
በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ልኡክ መሪ ኒኮላስ ቮን አርክስ “ኮሚቴው እስካሁን በረካታ ቁስለኞች በማስተናገድ ላይ ባሉትና በአማራ ክልል ለሚገኙት ለሰቆጣ፣ ደባርቅ፣ ወልድያ፣ ዳንግላ፣ መርሳ እና ላሊበላ አጠቃላይ ሆስፒታሎች፤ ለጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
እንዲሁም ከፍተኛ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት ላጋጠማቸው በትግራይ ክልል ለሚገኙ ለመቀለ፣ ውቅሮ፣ አዲግራት፣ ሽረ፣ መኾኒ እና ሸራሮ ሆስፒታሎች ቁሳቁሶችን ማቅረብን ጨምሮ ድጋች እየቀረቡ መሆኑን አስታውቀዋል።
በአፋር እና በሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በወለጋ በሚገኙ ዞኖች ለሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች ተመሳሳይ ድጋፍ መደረጉንም የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ልኡክ መሪ ኒኮላስ አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በኩል የተሰጡት አምቡላንሶች በተለይም ግጭቶች በተከሰቱባቸው ክልሎች ትልቅ ሚና ተጫወተዋልም ነው ያሉት የልኡኩ መሪ ኒኮላስ።