ናይጄሪያ በጥብቅ ትፈልገው የነበረውን የቦኮ ሃራም አዛዥ ያዘች
ናይጄሪያ “በጥብቅ እፈልጋቸዋለሁ” በሚል ከ5 ዓመታት በፊት የ100 የቦኮ ሃራም አባላትን ዝርዝር አውጥታ ነበር
ያው ሞዱ በጥብቅ ከሚፈለጉ የቡድኑ አዛዦች መካከል አንዱ ነበር ተብሏል
የናይጄሪያ ጦር፤ በጥብቅ ይፈልገው የነበረውን የቦኮ ሃራም ከፍተኛ አመራር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡
ጦሩ በጥብቅ እንደሚፈልጋቸው በቅርቡ ካስታወቃቸው የሽብር ቡድኑ አዛዦች መካከል እንደሆነ የተነገረለት ያው ሞዱ ቦርኖ በተባለው የሃገሪቱ ግዛት በተካሄደ ዘመቻ መያዙን የጦሩ ቃል አቀባይ ብ/ጄ ኦንዬማ ንዋቹኩ ተናግረዋል፡፡
የቦኮ ሃራም የሽብር ቡድን መሪ ክፉኛ መቁሰሉ ተሰማ
ቦርኖ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ጠንካራ ይዞታ እና መሸሸጊያ እንደሆነ ይነገራል፡፡
በዘመቻው የቡድኑን የፈንጂ ጦር መሳሪያዎች መጋዘን እና ፈንጂውን ለመስራት የሚጠቀምባቸውን ሰው ሰራሽ የማዳበሪያ ግብዓቶችን (ዩሪያ) በቁጥጥር ስር ማዋላቸውንም ነው ቃል አቀባዩ የተናገሩት፡፡
በናይጀሪያ ታጣቂዎች ት/ቤት ውስጥ በመግባት ተማሪዎችን አገቱ
በመንግስት የተቀመጠውን እገዳ በመተላለፍ ማዳበሪያውን ለቡድኑ ያቀርቡ ነበር የተባሉ ሁለት ግለሰቦችም በጦሩ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ወንዶችና ሴቶች የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩባት የናይጄሪያዋ ‘ኡባንግ’ መንደር
ናይጄሪያ በጥብቅ እፈልጋቸዋለሁ በሚል ከ5 ዓመታት በፊት የአንድ መቶ የቦኮ ሃራም አባላትን ዝርዝር በፎቶ ጭምር አስደግፋ አውጥታ ነበር፤ ምንም እንኳ ስለ ስኬታማነቷ ደፍረው የሚናገሩ ብዙዎች ባይኖሩም፡፡