በሀገሪቱ ፓርላማ ለእታ የቀረቡት "ዩፎዎች" 1 ሺህ አመት እድሜ እንዳላቸው ተገልጿል
ሜክሲኮ በምህጻረ ቃል “ዩፎ” የሚሰኙትን ምንነታቸው በውል የማይታወቅ በራሪ አካላት ህልውና በይፋ የገለጸች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።
ጋዜጠኛ እና “የዩፎ” ተመራማሪው ጄም ሙሳን ከሌሎች ምሁራን ጋር በመሆን ለሜክሲኮ ፓርላማ የሁለት ”ዩፎ”ዎች ቅሪት አካላትን ለእይታ አቅርበዋል።
በፈረንጆቹ 2017 በፔሩ ተገኝተዋል የተባሉት ሁለት በራሪ ፍጡራን 1 ሺህ አመት እድሜ እንዳላቸው በምርምር መረጋገጡም ተገልጿል።
ግኝቱ ይህቺን ምድር የሚጋሩ ሌሎች ፍጡራን ሳይኖሩ አይቀርም የሚሉ የቀደሙ መላምቶችን በሳይንሳዊ መንገድ ይበልጥ ያጠናከረ ነው ተብሏል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic