የኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኃላፊነት ተራዘመ
አሜሪካ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆምና ድርድር እንዲደረግ አፍሪካ ህብረትን እንደትደግፍ አስታውቃለች
ሙሳ ፋኪ መሃመትና ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ተወካይ ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ ተወያይተዋል
በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ኃፊነት መራዘሙን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት አስታውቀዋል።
የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በትዊተር ገጻቸው እንዳስታወቁት፤ የኃፊነት ጊዜያቸው የተራዘመውን የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ን ተቀብለው መናገራቸውን ገልጸዋል።
"በኦባሳንጆ ላይ ያለቸውን እምነት የገለጹት ሊቀ መንበሩ፤ በኢትዮጵያ በግጭት ውስጥ ላኩ ከሁለቱም ወገኖች እና ተዋናዮች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በመቀጠል በኢትዮጵያ እና በአከባቢው ሰላም እና እርቅ እንዲመጣ እንዲሰሩ ማበረታታቸውን አስታውቀዋል።
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በአዲስ አበባ ከሚገኙት የአሜሪካ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ አምባሳደር ማይክ ሀመር ጋር መወያየታቸውንም ገልፀዋል።
የአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያግዝ ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውንም አስታውቀዋል።
በተያያዘ የአሜሪካ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ አምባሳደር ማይክ ሀመር የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር በትናትናው እለት መክረዋል።
በውይይታቸውም ሁለቱም የአፍሪካ ቀንድ ተወካዮች በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለማካሄድ የታሰበው የሰላም ድርድርን አሜሪካ በምን መልኩ መደገፍ ትችላች የሚለው ላይ መምከራውም ታውቋል።
የህወሓት ከዚህ ቀደም በቃል አቀባዩ በኩል በሰጠው መግለጫ፤ በኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ላይ እምነት እንደሌለው እና የሚያመቻቹት ነገር ፍትሀዊ ውጤት ሊያመጣ አይችልም ያለ ሲሆን፤ ግለሰቡን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ህብረትም ሰላም አያመጣም ማለቱ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሓት ጋር የሚደራደር ቡድን ሰይሞ ስራ ማስጀመሩ የሚታወስ ሲሆን፤ ከህወሓት ጋር የሚደረገው ድርድር በአፍሪካ ህብረት ስር መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጿል።
ከህወሓት ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ ላይ የአፍሪካ ህብረትን አቋም የሚደግፉ ታዋቂ አፍሪካዊያን ቢሳተፉ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞ እንደሌለው ገልጾ ነበር።
ነገር ግን ከህወሃት ጋር ይደረጋል የተባለው ንግግር የሚመራው በአፍሪካ ሕብረት ብቻ እንደሆነ የፌደራል ምንግስት መግለጹ ይታወሳል።