በኢትዮጵያ አዲስ የመብት ጥሰቶች ምርመራ ይደረግ በሚል የተካሄደው የተመድ ልዩ ስብሰባ ተቃውሞ ገጠመው
ሃገራቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ግዛታዊ አንድነት እንዲሁም የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን መፈታታቸውን እንደሚደግፉም ነው ያስታወቁት
ስብሰባው እልባትን ከመስጠት ይልቅ መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ ይበልጥ የሚያባብስ ነው ሲሉ ተሳታፊ ሃገራቱ ተቃውመዋል
በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ባለው ጦርነት የተፈጸሙ ሰብዓዊ ጥሰቶች እንደገና በገለልተኛ ዓለም አቀፍ አካል ይመርመሩ በሚል የቀረበው ሃሳብ ከበርካታ ሃገራት ተቃውሞ ገጠመው፡፡
በአውሮፓ ህብረት ጠያቂነት የተካሄደው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ በጉዳዩ አግባብነት ላይ ጭምር ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡
ኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሃገራት ለመጪው አርብ የተቀጠረውን ስብሰባ ውድቅ እንዲያደርጉ ጠየቀች
ጦርነቱ በመቀጠሉ ምክንያት የሰብዓዊ መብት ችግሮች መክፈታቸውን የተናገሩት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክትል ኮሚሽነር ናዳ አል ናሽፍ በተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ጋዜጠኞችንና የተመድ ሰራተኞችን ጨምሮ በርካቶች ተለይተው እየታሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ብዙዎቹ የታሰሩበት ምክንያት እና ቦታ በውል አለመታወቁ አሳሳቢ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡
ይህ መቆም እንዳለበት በማስታወስም የዜጎች መብት ሊጠበቅና ተጠያቂነት ሊኖር እንደሚገባ አሳስበዋል፤ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጥምረት መስራቱና በትግራይ እና በሌሎችም አካባቢዎች የተፈጸመውን መመርመሩ እንደሚቀጥል በመጠቆም፡፡
በጣሊያን ወረራ ጊዜ ጭምር እንዲህ ዐይነት ፈተና የገጠማት ኢትዮጵያ በድጋሚ በምክር ቤቱ ፊት ተለይታ እንድትቆም መገደዷን የተናገሩት በጄኔቭ የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ዘነበ ከበደ ምክር ቤቱ የማይመለከተውን ፖለቲካዊ ጉዳይ ለማየት መሰብሰቡን አጠይቀዋል፡፡
በአዲስ የቅኝ ገዢ አስተሳሰቦች ተጠልፏል ያሉትን የባለ ብዙ ወገን ግንኙነት ለመጠበቅ ኢትዮጵያ አሁንም ከሃገራት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛ እንደምትሰራ አስታውቀዋል፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተመሳሳይ የቅኝ ግዛት ዘመን ኃይሎች አሁንም ከብዙ ሃገራት ቀውስ ጀርባ የመሆናቸው ተግባር መቆም እንዳለበት በማሳሰብ፡፡
በሽብርተኛው ህወሓት በአማራ እና በአፋር ክልሎች የፈጸማቸውን አስከፊ ሰብዓዊ ጥሰቶች ያላወገዘው ምክር ቤቱ በጣምራ የተመረመረውን ጉዳይ ለምን በድጋሚ መመርመር እንደፈለገ በመጠየቅም ኮሚሽኑን አሁንም በጣምራ በሁለቱ ክልሎች የተፈጸመውን እንዲመረምር ጋብዘዋል፡፡
እንዲህ ዐይነቱ አካሄድ ሁኔታዎችን የበለጠ ከማባባስ ያለፈ ጥቅም የለውምም ብለዋል አምባሳደር ዘነበ፡፡
ከዚህ ይልቅ ምክር ቤቱ የተጀመሩ ሃገራዊ ጥረቶችን እንዲደግፍ ጠይቀዋል፡፡
በልዩ ስበሰባው የተሳተፉ የአፍሪካ ሃገራት ቡድን አባላት በኢትዮጵያም ይሁን በአፍሪካ ህብረት የተጀመሩ ጥረቶችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ሲሉ የቀረበውን ሃሳብ ሳይደግፉ ቀርተዋል፡፡
የካሜሩን ተወካይ
ጉዳዩን ፖለቲካዊ መልክ ማስያዝ እና ምክር ቤቱም በእንዲህ ዐይነቱ ጉዳይ መግባቱን እንደማይጠቅም በማስታወስም ሊቆም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነትና ሉዓላዊነት መጠበቅ እንደምትደግፍ ያስታወቀችው ሩሲያ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ እንደሚገባቸውና የተጀመሩ የሽምግልና ጥረቶችን እንደምትደግፍ አስታውቃለች፡፡
ኢሰመኮ፤ የአውሮፓ ህብረት ባቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ስጋቱን ገለፀ
ደቡብ ኮሪያ፣ አርጀንቲና፣ ህንድን እና ቻይናን መሰል የልዩ ስብሰባው ተሳታፊዎችም ይህንኑ ሃሳብ ደግፈዋል፡፡
ቬንዙዌላ በሃገራት ጉዳይ ጣልቃ መግባት ሉዓላዊነታቸውንም መዳፈር ነው በሚል ተቃውማለች ስብሰባው የማይጠቅም ጭምር እንደሆነ በማከል፡፡
የቬንዙዌላ ተወካይ
አካሄዱ ፖለቲካዊ ግፊት እንዳለበት ያስታወቀችው ኩባ በበኩሏ አካሄዱ መሬት ላይ ያሉ ሁኔታዎች ከማባባስ በተለየ የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ገልጻለች፡፡
ኦስትሪያን መሰል ሃገራት ገለልተኛ ዓለም አቀፋዊ አካል እንዲቋቋም በአውሮፓ ህብረት የቀረበውን ሃሳብ ደግፈዋል፡፡