“ኢትዮጵያን ለመንካት የሚሞክሩ ካሉ አሳፍረን እንመልሳለን፤ ይህን ማድረግ የሚያስችል በቂ አቅም አለን”- ጠ/ሚ ዐቢይ
ጠ/ሚ ዐቢይ “በቀይ ባህር ላይ የባህር በር ማግኘት የኢትዮጵያ የማይናወጥ ብሄራዊ ጥቅም ነው፤ ይህን ዓለም ዛሬ ሊሰማው ይገባል” ብለዋል
“ከኤርትራ ጋር ተያይዞ ከዛ የከፋ ነገር እስካልመጣ በእኛ ተነሳሽነት በኤርትራ ወንድሞቻችን ላይ ምንም ነገር አይፈጸምም” ብለዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ኢትዮጵያን ለመንካት የሚሞክሩ ካሉ አሳፍረን እንመልሳለን፤ ይህን ማድረግ የሚያስችል በቂ አቅም አለን” አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሲሰጡ በቀይ ባህር እና በምስራቅ አፍሪካ ውጥረት ዙሪያ አስተያየት ሰጥተዋል።
ከባህር በር ጋር በተያያዘ ባነሱት ሀሳብ “ከሶማሊ ላንድ ጋር ባደረገነው የመግባቢያ ስምምነት፤ ኢትዮጵያን የሶማሊያን ግዛት ለመውሰድ ትስማማች የሚል ነው የተወራው፤ እኛ 99 ዓመት ጠይቀን እምቢ ብለውን ለ50 ዓመት ሊዝ ነው የተስማማነው” ብለዋል።
“የ50 ዓመት ሊዝ እንዴት ነው መሬት መቀማት የሚሆነው፤ እኛ ከሶማሊያ ቀጥሎ ትልቁን የሶማሌ ህዝብ ያለባት ሀገር ነች ኢትዮጵያ፤ ከሶማሊያ ጋር ምንም አጀንዳ የለንም” ሲሉም ተናግረዋል።
“ከምጽዋ እነከ ሶማሊያ 5 ሺህ ኪሎ ሜትር ነው የባህር ክልሉ፤ ልናማው አልቻልንም፤ ሌሎች ናቸው ከሌላ ቦታ እየመጡ እንደፈለጉ እያደረጉት ያሉት፤ ትንሽዬ የባህር በር እና መተማመኛ ስጡነ ነው ያልነው፤ ጥያቄያችን ይህ ነው” ብለዋል።
ከኤርትራም ይሁን ከጂቡቲ፣ ከሶማሊያ እና ከኬንያ ጋ ለኢትዮጵያ የሚያዋጣት ሰላማዊ ጉርብትና እና በሰጥቶ መቀበል አብሮ ማደግ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
“እኛ ሀገር መገንባት የምንፈልግ አርበኞች እንጂ ለየትኛውም አካል በስሙኒ ተገዝተን አጀንዳ የምናራግብ አይደልንም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ይህንን አክብሮከሚመጣ ሀገር ጋር በደስታ አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነን” ብለዋል
ሰሞኑን ከኤርትራ ጋር ተያይዞ በሚነሱ ጉዳዮች ላይም “እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው፤ “ከኤርትራ በኩል የከፋ ነገር ካመጣ በስተቀር በእኛ ተነሳሽነት በኤርትራ ወንድሞቻችን ላይ ምንመ ነገር አይፈጸምም” ሲሉም ተናግረዋል።
“በሶማሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንን ለጋራ ሰላም ብለን ገብረናል፤ አሁንም የምንፈልገው ይህንን ነው፤ ሶማሊያ አሁንም እንዲረጋጉ እና ቀልብ እንዲገዙ ጊዜ ሰጥተናል፤ እንታገሳለን” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በንግግራቸው።
“የኢትዮጵያን የማይናወጥ ብሄራዊ ጥቅም ዓለም ዛሬ ሊሰማው ይገባል” ባሉት ንግግራቸውም “ኢትዮጵያ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በቀይ ባህር ላይ የባህር በር ያስፈልጋታል፤ በዚህ ጉዳይ ወደ ኋላ የማይል ይፋዊ አቋም አለን” ብለዋል።
ነገር ግን “ይህን ለማሳካት ጦርነትም ሆነ የኃይል አማራጭ አንፈልግም፤ ፍላጎታችንን ማሳካት የምንሻው በሰላማዊ አማራጭ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
“ይህ ምክንያታዊና ፍትሃዊ ጥያቄ ነው፤ እኛ ባናሳካው ልጆቻችን ያሳኩታል፤ ኢትዮጵያ የትኛውንም ሀገር ላይ ወረራም ሆነ ጥቃት አትፈጽምም፤ ነገር ግን ኢትዮጵያን ለመንካት የሚሞክሩ ካሉ አሳፍረን እንመልሳለን፤ ይህን ማድረግ የሚያስችል በቂ አቅም አለን።
“ስንገዛ ከነበሩ መሳሪያዎች በተጫመሪ በውጊያ ክፍተት የገጠሙንን ነገሮች ማምረት ጀምረናል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ “እናመርታለን፣ ሰው አለን፣ ጀግኖች ነን፣ ሰው አንነካም፣ ከነኩን ግን ለማንም አንመለስም” ሲሉ አሳስበዋል።
ህዳሴ ግድብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በንግግራቸው ስለ ህዳሴ ግድብም ያሰኑ ሲሆን፤ “አሁን ላይ ግድቡ አልቋል፤ ከግድቡ ላይ የሚያልፍ ድልድይ አሁን ተገጥሞ ተጠናቋል” ብለዋል።
“ህዳሴ ግድብ ለሱዳን አና ለግብጽ ትልቅ ድል ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ “ውሃው ሲያዝ ችግር ሊያጋጥም ይችላል በሚል ስጋት ነበረ፤ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ምን ችግር ሳይፈጠር ውሃ ይዘን ግድቡን ጨርሰናል” ብለዋል።
“ከዚህ በኋላ ግብጽ ወይም ሱዳን የውሃ ችግር ቢያጋጥማቸው ሲቸገሩ ማየት አንችልም፤ ውሃ ስላለን ልንለቅላቸው አንችላልን” ሲሉም ተናግረዋል።
ባለፉት 5 ዓመታት የህዳሴ ግድብ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ተዋጣው ገንዘብ ብቻ ሳይሆን፤ በሺህ የሚቆጠር የሰው ህይወት ተገብሮበታል ብለዋል።
የግድቡ ግንባታ እንዲስተጓጎል ያላስታጠቁበን ሰው የለም፤ ነገር ግን የግድቡን ግንባታ ማቆም ሰላማይቻል፤ ተዋግን ነው ግድቡን የሰራነው ብለዋል።