የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ደገፈ
ኢትዮጵያ በቀይ ባህርን የወደብ አማራጮችን የሚያሰፋ የመግባቢያ ሰነድ ከሶማሊላንድ ጋር መፈራረሟ ይታወቃል
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት “ለስምምነቱ ውጤታማነት በጋራ በመቆም ሚናችንን እንወጣለን” ብሏል
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ እንደሚደግፍ አስታወቀ።
ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፤ በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ መካከል ወደ ብን አስመልክቶ በተደረገው የመግባቢያ ስምምነት ዙሪ መምከሩን አስታውቋል።
- ኢትዮጵያ ወደብ እንድትከራይ እና በምላሹ ለሶማሊላንድ እውቅና እንድትሰጥ ስምምነት ላይ መደረሱን ሶማሊላንድ አስታወቀች
- የኢትዮጵያን ቀይ ባህርን የመጠቀም ፍላጎት ያሳካል የተባለ የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን መንግስት ገለጸ
በዚህም በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረመውን " መግባቢያ ሰነድ" በተመለከተ የስምምነቱን ማዕቀፍ ፣ዝርዝር ይዘቱን እና ከስምምነቱ ጋር ተያይዞ ባሉት እድሎችና ስጋቶች ላይ በዝርዝር መወያየቱን አስታውቋል።
ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በመግለጫው፤ “ስምምነቱን ያለልዩነት የምንደግፍ መሆናችንን አረጋግጠናል” ብሏል።
“የመግባያ ስምምነቱ ከተግባራዊነቱ አንፃር የሚኖሩትን ውስጣዊ እና ውጫዊ ስጋቶችን እንዲሁም እድሎችን በዝርዝር በመምከረም ለስምምነቱ ውጤታማነት በጋራ በመቆም ሚናችንን ለመወጣት ያለንን ቁርጠኝነት ዳግም እናረጋግጣለን” ብሏል ም/ቤቱ በመግለጫው።
መንግስት ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መላው የሀገሪቱ ህዝብ ለስምምነቱ መሳካት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡመረ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪ አቅርቧል።
ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን የመጠቀም ፍላጎቷን ለማሳካት መንገድ የሚጠርግ እና የወደብ አማራጮችን የሚያሰፋ የመግባቢያ ሰነድ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ላይ ትናንት መፈራረሟ ይታወሳል።
ስምምነቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የሶማሌ ላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ,ባሳለፍነው ሳምንት ተፈራርመዋል።
በኢትዮጵያና እና የሶማሊላንድ መካከል የተፈረመው ስምምነት ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ በሊዝ ወታደራዊ ካምፕ እንድታገኝ እና የባህር ላይ የንግድ እንቅስቃሴ እንድታደርግ መንገድ የሚከፍት ነው ተብሎለታል።
በምላሹ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ እውቅናን እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ እንደምትወስድ ተገልጿል።
በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረመውን ስምምነት የተቃወመችው የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የደረሰችውን የወደብ ሰምምነት "ውድቅ የሚያደርግ" ህግ መፈረማቸው ተዘግቧል።