ፕሬዝዳንቷ ተማሪዎቹ ደህንነት በሚጠበቅበት ጉዳይ ላይ ነው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዘዳንት ጋር የተወያዩት
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ክልል መውጣቱን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዘዳንት ጋር ተወያዩ፡፡
ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ የማህበሩ የበላይ ጠባቂ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንቷ በትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ደህንነት ስለሚጠበቅበት መንገድ ከማህበሩ ፕሬዘዳንት አቶ አበራ ቶላ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ ለተጎዱ ወገኖች በተለይም ለህጻናት ሴቶች እና አረጋዊያን ቀደም ሲል ይደረግ የነበረው ድጋፍ እንዳይስተጓጉል በሚሉ ፍሬ ሐሳቦች ላይ ማተኮሩንም ነው የፕሬዝዳንቷ ጽህፈት ቤት ያስታወቀው።
ጽህፈት ቤቱ ገለጻ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሰብዓዊ እንቅስቃሴውን ይበልጥ እንዲያጠናክር፣ ለሌሎች አቻ ተቋማት አጋር እና ምሳሌ እንዲሆንም ፕሬዘዳንቷ አደራ ብለዋል።
አቶ አበራ ቶላ በበኩላቸው ማህበሩ እያደረገ ስላለው ተግባር ለፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ አብራርተዋል።
በክልሉ የሚገኙትን ተማሪዎች በቀይ መስቀል በኩል ለማስወጣት መንግስት አስፈላጊዉን ትብብር እንደሚያደርግ ዛሬ ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡