ቭላድሚር ፑቲን ገለልተኛ አጣሪዎች ወደ ዛፖሮዚያ ኒውክለር ጣቢያ እንዲሄዱ ፈቃድ ይሰጣቸዋል አሉ
ተመድ በዩክሬን የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አካባቢ ከጦር ነጻ ቀጠና እንዲቋቋም ጠይቋል

ሩሲያ እና ዩክሬን በኑክለር ጣቢያው ጥቃት በማድረስ እርስበእርሳቸው እየተካሰሱ ነው
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ ገለልተኛ አጣሪዎች ጦራቸው ወደያዘው የዛፖሮዚያ ኒዩክለር ጣቢያ እንዲሄዱ ፍቃድ ይሰጣቸዋል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የዛፖሮዚያ ኒውክለር ጣቢያ በተቆጣጠረው የሩሲያ ጦር እና በዩክሬን ኃይሎች መካከል በጣቢያው ጉዳት በማስከተል ትልቅ አደጋ ያስከትላል ሲል ተመድ በተደጋጋሚ ሲያሳስብ ቆይቷል
- ሩሲያ የአውሮፓ ሀገራት የተፈጥሮ ጋዝ የሚያገኙበትን ማስተላለፊያ ለሶስት ቀናት ልትዘጋ ነው
- ተመድ በዩክሬን የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አካባቢ ከጦር ነጻ ቀጠና እንዲቋቋም ጠይቋል
የሩሲያ ቤተ መንግስት (ክሬምሊን) ፕሬዝዳንት ፑቲን እና የፈረንሳዩ አቻቸው ውይይት ካደረጉ በኋላ አጣሪዎች እንዲገቡ እንደሚፈቀድላቸው ተናግረዋል፡፡
የቡድን ሰባት አባል ሀገራት የሩሲያ ጦር ከኒውክለር ማብላያ ጣቢያው እንዲለቅ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ነበር፡፡
ተመድ በዩክሬን የኃይል ማመንጫ ጣቢያ አካባቢ የደረሰው ጥቃት በአካባቢ ከጦር ነጻ ቀጣና ይኑር የሚል ጥሪ ለማድረግ እንዳስገደደው መግለጹ ይታወሳል፡፡
ሩሲያ እና ዩክሬን ከአውሮፓ ትልቅ የሆነውን እና በዩክሬን የሚገኘውን የኑክሊየር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ጥቃት በማድረስ እርስ በእርሳቸው በመካሰስ ላይ ባሉበት ወቅት ተመድ ከጦር ነጻ ቀጣና እንዲቋቋም ሀሳብ ማቅረቡን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በደቡባዊ ዩክሬን የሚገኘው እና ሩሲያ በዩክሬን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” እንደጀመረች በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር የዋለው የዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጥቃት ደርሶበታል ተብሏል፡፡