የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አጠቃላይ የምርጫ ውጤትን ይፋ አድርጓል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አጠቃላይ የምርጫ ውጤትን በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ በዛሬው እለት በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ እንዳስታወቀው፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች ቅሬታን ድጋሚ ምርጫ እና ድጋሚ ውጤት ቆጠራ እንዲካሄድ መወሰኑን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ሴኔ 14 ፣2013 በተካሄደው ምርጫ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች ያቀረቡት ቅሬታ ከመረመረ በኋላ በ10 የምርጫ ክልሎች የተካደው ምርጫ እንዲሰረዝና በድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ምርጫ ቦርድ ወስኗል።
ቦርዱ በድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ከወሰነባቸው 10 የምርጫ ክልሎች ውስጥ በአማራ ክልል መርጦለማሪያም፣ አዴት፣ ባቲ፣ ሞላሌእና ራያ ቆቦ ይገኙበታል።
በአፋር ክልል ዳሎል የምርጫ ክልል፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንጊ የምርጫ ክልል፣ እንዲሁም ደቡብ ክልል መስቃን ማረቆ፣ ቡሌእና ባስኬቶ የምርጫ ክልሎች ናቸው ምርጫ ው የሚካሄደው።
ቦርዱ ምርጫ ድጋሚ እንዲካሄድ ከመወሰን በተጨማሪ 10 የምርጫ ክልሎች ድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄ መወሰኑንም አስታውቋል።
ድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድባቸው ከተወሰኑ የምርጫ ውጤቶች ውስጥም 3ቱ የህዝብ ተወካች ምር ቤት መሆናቸውን ነው ሞርዱ ያስታወቀው።
ኢትዮጵያ 6ኛ ዙር የተወካዮች ምክርቤትና የክልል ምክርቤት ተወካዮች ምርጫ፤ የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ሰኔ 14፣2013 መካሄዱ ይታወሳል።
ምርጫ በ673 የምርጫ ጣቢያዎች በአዲስ አበባን ጨምሮ በክልሎች ተካሂዷል፤ በሶማሌ ክልል ከምርጫ ቁሳቁስ ህትመት ጋር በተያያዘ እንዲሁም በትግራይ ክልል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ምርጫ 2013 አልተካሄደም።
የሶማሌ ክልልና በተለያየ ምክንያት ምርጫ የማይሰጥባቸው ምርጫ ጣቢዎች ጳጉሜ 1 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል።