የሩሲያ በዩክሬን ዛፖሪዝሂያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሁለት ከተሞች መያዙ ተገለፀ
የሞስኮ ኃይሎች ወደ ኦሪኪቭና ሁሊያይፖሌ ከተሞች እየገቡ እንደሆነ ተመላቷል
ዛፖሪዝሂያ ግንባር ለወራት ጋብ ብሎ የነበረው ውጊያው ተባብሶ መቀጠሉን ተነግሯል
የሩሲያ ጦር በዩክሬን ደቡባዊ አቀጣጫ በምትገገኘው ዛፖሪዝሂያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሁለት ከተሞች መያዙ ተገለፀ።
ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን መላኳን ተከትሎ ጦርነት ከተጀመረ አንድ ዓመት ሊሞላው አንድ ወር ብቻ ቀርቶታል።
አሁንም በቀጠለው ውጊያው ወደ ኋላ አፈግፍገው የነበሩት የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ውስጥ የሚገኑ ከተሞችን መልሰው መቆጣጠር መጀመራቸው ተነግሯል።
ዛፖሪዝሂያ ግንባር ለወራት ጋብ ብሎ የነበረው ውጊያው ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎም የሩሲያ ኃሎች በክልሉ ወደሚገኙ ኦሪኪቭ እና ሁሊያይፖሌ ከተሞች እየገቡ እንደሆነ ተመላቷል።
በዛፖሪዝሂያ ክልል ውስጥ በሩሲያ የተሾሙት ባለስልጣን ቭላድሚር በሁለት ከተሞች ዙሪያ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እና የሩሲያ ጦር ከተሞቹን እየተቆጣጠረ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የሩሲያ ጦርም በዛፖሪዝሂያ ክልል ውስጥ በከፈተው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ቁልፍ የሆኑ ስፍራዎችን በመቆጣጠር ላይ መሆኑን ለተከታታይ ሁለት ቀናት አስታውቋል።
የሩሲያ ጦር ባሳለፍነው ሳምንት የዩክሬኗን የማዕድን ከተማ ሶሌዳርን መቆጣጠሩን ማሳወቁይ ይታወሳል።
የሩሲያ የመከላከያ ሚንስቴር ሶሌዳር የተያዘችው በሚሳኤልና በመድፍ መሳሪያዎች በጠላት ላይ ባደረገው የማያቋርጥ የቦምብ ጥቃት ነው ብሏል።
ኪየቭ እና ምዕራባውያን የከተማዋን ጠቀሜታ ዝቅ ቢያደርጉትም የሩሲያ ጦር ግን ግን ከተማዋን መያዙ በአቅራቢያ ወደምትገኘው ወደ ባክሙት ከተማ የሚወስዱትን መንገዶች ለመቁረጥ እና የቀሩትን የዩክሬይን ኃይሎች ለማጥመድ ያስችላል ብሏል።