ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ የሚገኙ የምአራባውያን ጄነራሎችን አጠፋለሁ ስትል ዛተች
በዩክሬን የሚገኙ የውጭ ሀገራት ቅጥረኛ ተዋጊዎችንም እንደማትምር ሩሲያ አስታውቃለች
ሩሲያ፤ ዩክሬን የውጭ ሀገራት የጦር ጄነራሎች የሲቪል መሰረተ ልማቶችን ለውጊያ እንዲጠቀሙ አድርጋለች ስትል ከሳለች
ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ እየተዋጉ ያሉ የምእራባውያን ጦር ጄነራሎችን እንደምታጠፋ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ላቭሮቭ አስታወቁ።
ሰርጌ ላቭሮቭ በኦንላይን በሰጡት ብራሪያ፤ ሩሲያ ከምእራባውያን ጦር ጄነራሎች በተጨማሪ በዩክሬን የሚገኙ የማንኛውም የውጭ ሀገራት ቅጥረኛ ተዋጊዎችንም እንደማትምር አስታውቀዋል።
ዩክሬን የውጭ ሀገራት የጦር ጄነራሎች የሲቪል መሰረተ ልማቶችን ለውጊያ እንዲጠቀሙ አድርጋለች ሲሉም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ላቭሮቭ ከሰዋል።
በሩሲያ በኩል ንጹሃን ዜጎችን እንደ ምሽግ መጠቀም ምንመ አይነት ማረጋገጫ የለም ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ በዩክሬን በኩል ግን የምእራባውያን ጄነራሎችና ቅጥረኛ ተዋጊዎች ሲቪሊያንን እና የሲቪሊያን መገልገያዎችን እንደ ምሽግ እንዲጠቀሙ ተደርጓል፤ ይህ ዓለም አቀፉን ህግ የሚጻረር ነው ብለዋል።
ሩሲያ የሲቪል መሰረተ ልማቶችን መሸሸጊያ አድርገው ሩሲያን የሚዋጉ የውጭ ሀገራት ጄነራሎችና ቅጥረኛ ተዋጊዎችን ካገኘች ታጠፋለች ሲሉም ላቭሮቭ ዝተዋል።
ሩሲያ በፈረንጆቹ በየካቲት 2022 "ልዩ ተልዕኮ" በሚል ነበር ዩክሬን ላይ ዘመቻ የጀመረችው። በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል የተባለው ጦርነት ግን አሁን ላይ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።
የዩክሬን ወታደሮች በሩስያ ጦር ላይ ባደረጉት የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ በሁሉም አቅጣጫ እየገፉ መሆናቸውን የመከላከያ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ሩሲያ የኪየቭን ግኝት በማጣጣል ጦሯ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ነው ብላለች።