ከዩክሬን ከተነሱት ድሮኖች ውስጥ አንዱም ኢላማውን አልመታም ተብሏል
ሩሲያ ከዩክሬን ተነስተው ጥቃት ሊሰነዝሩ የነበሩ ድሮኖቸን በአየር ላይ ማምከኗን አስታወቀች።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳታወቀው፤ የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ስርዓት ከዩክሬን የተነሱ ድሮኖችን አየር ላይ ማውደሙን አስታውቋል።
ከዩክሬን ተነስቶ ኢላማውን የመታ አንድም ድሮን እንደሌላ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በቴሌግራም ገጹ አስታውቋል።
- የሩሲያ ጦር መሳሪያዎች “እንደ ኬክ” እየተሸጡ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ
- ሩሲያ በቀጣዮቹ አምስት ዓመት ውስጥ ከኔቶ ጋር ጦርነት ልትጀምር እንደምትችል ተገለጸ
በቤልግሮድ ክልል ጉብኪን ከተማ በነበረው የደሮን ጥቃት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም የተባለ ሲሆን፤ ነገር ግን አየር ላይ የተመቱ ድሮኖች ስብርባሪ አራት ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ተነግሯል።
ዩክሬን እስካሁን ስለ ድሮን ጥቃቱ የሰጠችው አስተያየት የለም።
ቤልጎሮድ እና ሌሎች የዩክሬን የሚያዋኑ ክልሎች ሁለት ዓመታትን ባስቆጠረው ጦርነት በርካታ ጊዜ ከዩክሬን ሃይሎች ጥቃት ይደርስባቸዋል።
ኪየቭ በክልሎቹ ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በሩሲያ ወታደራዊ እና የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ላይ ማነጣጠራቸውን እና ይህም የሞስኮን አጠቃላይ ወታደራዊ አቅም እንደሚጎዳ ተናግራለች።
ሩሲያ በፈረንጆቹ በየካቲት 2022 "ልዩ ተልዕኮ" በሚል ነበር ዩክሬን ላይ ዘመቻ የጀመረችው። በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል የተባለው ጦርነት ግን አሁን ላይ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።