ሩሲያ ከባህር ላይ በተኮሰችው ሚሳዔል የዩክሬን ጦር መሳሪያ መጋዝን ማውደሟን አስታወቀች
ሩሲያ መጋዘኑን ለማውደም ካሊበር የተባለ ሚሳዔል መጠቋም አስታውቋለች
ከወደሙ የጦር መሳሪያዎች ውስጥ የአሜሪካ ሂምራስ ሮኬትና ሌሎች ከምእራባውያን የተለገሱ የጦር መሳሪያዎች ይገኛሉ
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ከባህር ላይ በተኮሰው ሚሳዔል በዩክሬን ኦዴሳ ክልል የሚገኝ ጦር መሳሪያ መጋዝን ማውደሙን አስታወቀ።
የሩሲያ ጦር ካሊበር የተባለ ሚሳዔል የተጠቀመ ሲሆን፤ በጥቃቱምበመጋዝኑ ውስጥ የነበረ አሜሪካ ሰራሹ ሂርማስ (HIMARS) የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሮኬቶችን ማውደሙን አስታውቋል።
በተጨማሪም በመጋዘኑ ውስጥ የነበሩ እና ምዕራባውያን ለዩክሬን የለገሷቸው የፀረ አውሮፕላን መሳሪያዎችን ማውደሙንም አስታቋል።
በተጨማሪም በኬህርሶን ክልል በተካሄደ ውጊያ ሁለት M777 መድፎችን ማውደሙን ያስታወቀ ሲሆን፤ እንዲሁም በዛፖሪዝያ ክልል ደግሞ 100 ቶን ነዳጅ የያዘ ዲፖ ማውደሙን አስታቋል።
ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በመለገስ ላይ ሲሆኑ፤ ሩሲያም የተለገሱትን የጦር መሳሪያዎች በማውደም ላይ መሆኗን ገልጻለች።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሐምሌ 16 በወሰደው እርምጃ ከ100 በላይ አሜሪካ ሰራሽ "HIMARS" ሮኬቶችን ማውደሙን ማስታወቁ ይታወሳል።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዳይለግሱ አሳስበው ልገሳቸውን ከቀጠሉ ግን እርምጃ መውሰዴን እንደሚቀጥሉማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ይፋዊ ጦርነት ከጀመረች ከተጀመረ 179 ቀናት ተቆጥረዋል።