የሩሲያ የጦር አውሮፕላን በዘመቻ ላይ የነበረን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ወደ ዋና ማዘዣው እንዲመለስ አስገድዳለች ተብሏል
ሩሲያ የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላንን ተልዕኮ ማስተጓጎሏ ተገለጸ።
ሩሲያ እና አሜሪካ በወታደራዊ ፍጥጫ ውስጥ ሲሆኑ በሶሪያ ምድርም እየተፎካከሩ ይገኛሉ።
ከሰሞኑም የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን እስላሚክ ስቴት በተሰኘው የሽብር ቡድን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ዘመቻ ላይ ነበሩ።
በዚያው ሶሪያ ያለው የሩሲያ ሱ-35 የተሰኘው የጦር አውሮፕላን ላይ ጉዳት በማድረስ ከዘመቻው መስተጓጎሉን ሲኤንኤን ዘግቧል።
የሩሲያ ሱ-35 እና ሱ-34 የተሰኘ የውጊያ አውሮፕላኖች ባሳለፍነው ቅዳሜ ከአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ጋር በቅርብ ርቀት በመብረት ጉዳት ማድረሳቸውም ተገልጿል።
ባሳለፍነው መጋቢት የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን በጥቁር ባህር አቅራቢያ እየበረረ እያለ በሩሲያ ጦር አውሮፕላን ተጠግቶ በመብረር በረራውን ማቋረጡ ይታወሳል።
በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ አየር ኃይል አዛዥ ጀነራል አሌክስ ግሪንኬዊች እንዳሉት የሩሲያ ጦር አብራሪዎች በሶሪያ እያደረጉት ባለው ዘመቻ ላይ እንቅፋት ሆነዋል ብለዋል።
አሜሪካ እና ሩሲያ በሶሪያ የተለያየ አላማ አላቸው ያሉት አዛዡ ሩሲያ የፕሬዝዳንት በሽር አላሳድን ስልጣን ማስጠበቅ እንደሆነም ተናግረዋል።
የአሜሪካ ተልዕኮ ግን አይኤስ የተሰኘውን የሽብር ቡድን ማጥፋት መሆኑንም አዛዡ ጠቅሰዋል።
ሩሲያ ከዚህ በፊት በሶሪያ የአየር ላይ ልምምድ እንደምታደርግ ገልጻ የሰው አልባ አውሮፕላን ስምሪቶች እንዳይኖሩ ማስጠንቀቋ ተገልጿል።