“ሞስክቫ” የተሰኘችው የሩሲያ ግዙፍ የጦር መርከብ በጥቁር ባሕር ላይ ሰመጠች
“ሞስክቫ” የሰመጠችው በፍንዳታ ከተጎዳች ከሰዓታት በኋላ መሆኑን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል
የዩክሬን ወታደራዊ ባለስልጣናት “ሞስኮቫ” መርከብን ኔፕቱን በሚባል ሚሳኤል “የመታናት እኛነን” እያሉ ነው
የሩሲያ ብሔራዊ አርማና ብሔራዊ ኩራት ተደርጋ የምትወሰደው ግዙፏ የጦር መርከብ “ሞስኮቫ” በጥቁር ባሕር መስመጧን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
‘ሞስክቫ’ የመስመጥ አደጋ ያጋጠመት፤ ባሳለፍነው ረቡዕ ዕለት በፍንዳታ ከተጎዳች ከሰዓታት በኋላ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ሚኒሰቴሩ "መርከቧ ካጋጠማት ፍንዳታ በኋ መጠነኛ ጥገና ተደርጎላት ወደ ወደብ አቅጣጫ እየተጎተተች ሳለ ሚዛኗን በማጣቷ ልትሰምጥ ችላለች " ማለቱም የሩሲያ መንግስት የዜና ወኪል ታስ ዘግቧል።
ዝርዝር ነገሮች ከመግለጽ የተቆጠበው ሚኒስቴሩ፤ አደጋው ሲከሰት በመርከቧ የነበሩ የ510 ሰራተኞች ህይወት የማዳን ስኬታማ ርብርብ ተደርጎ ፤ሁሉም መርከበኞች በጥቁር ባህር ላይ ከመርከቧ አቅራቢያ ወደነበሩ ሌሎች የሩሲያ የጦር መርከቦች መዘዋወራቸውንም ጠቅሷል።
ሞስኮ መረከቡ የመስመጥ አደጋ እንዳገጠመው ብትገልጽም፤ ኪቭ የጦር መርከቡ የተመታው በኔ ሚሳኤሎች ነው እያለቸው ነው፡፡
የዩክሬን ወታደራዊ ባለስልጣናት “ሞስክቫ በዩክሬን በተሰራ ኔፕቱን ሚሳኤሎች ነው የተመታቸው” ብለዋል።
ኔፕቱን ሚሳኤል፤ እንደፈረንጆቹ 2014 ሩሲያ ክሬሚያን በስሯ ካደረገቸው በኋላ ዩክሬን ከሩሲያ ባህር ኃይል ሊቃጣባት የሚችልን ጥቃት ለምግታት በማለም የሰራቸው ሚሳዔል ነው።
አንድ ከፍተኛ የዩክሬን ባለስልጣን 510 በሚደርሱ የመርከቧ ሰራተኞች ላይ የደረሰ ጉዳት ሊኖር እንደሚችልም ተናግረዋል።
12 ሺ 490 ቶን በሚገመተው በሞስክቫ መርከብ ላይ የደረሰው ጥቃት በዩክሬን ወታደራዊ ኃይል መፈፀሙ ከተረጋገጠ፤ ሞስኮቫ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በጠላት እርምጃ የሰመጠች ትልቁ የጦር መርከብ ትሆናች ነው የተባለው።
ከዚህም በተጨማሪ፤ ሩሲያ በዩከሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ያጣችው ሁለተኛው ትልቅ መርከብ ይሆናል።
ሩሲያ በዩክሬን አዞቭ ወደብ ላይ የነበረውና ለተዋጊ አውሮፕላን ማረፊያ አድርጋ ትጠቀምበ ትሳራቶቭ የተሰኘ መርከብ በመጋቢት ወር ከዩከሬን ወታደራዊ ኃይሎች በተሰነዘረ ጥቃት እንደወደመባት ይታወሳል።