ሳዑዲ በአገሯ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መላኳን ካጠናቀቀች በኋላ አዲስ ቪዛ መስጠት እንደምትጀምር ገለጸች
ሳዑዲ አረቢያ ብሔራዊ በዓሏን በማክበር ላይ ትገኛለች
ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ከ45 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል
ሳዑዲ በአገሯ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መላኳን ካጠናቀቀች በኋላ አዲስ የስራ ቪዛ መስጠት እንደምትጀምር ገለጸች።
በርካታ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመጓዝ በተለያዩ የሙያ መስኮች የሚሰማሩባት አገር ናት።
በነዳጅ የበለጸገችው ይህች የመካከለኛው ምስራቅ አገር የሄዱ ኢትዮጵያዊያን የተሻለ ገቢ እያገኙ ህይወታቸውን ለውጠዋል።
ይሁንና ላለፉት ወራት በሳውዲ ይሰሩ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በሳውዲ አረቢያ መንግስት ተይዘው ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል። አሁንም በርካታ ኢትዮጵያውያን ችግር ላይ እንዳሉ ይናገራሉ፡፡
ኢትዮጵያውያንንን ጨምሮ በርካቶች ይቸገሩበት ነበር የተባለለት የሳዑዲ የ“ከፋላ” ስርዓት ተቀየረ
የሳዑዲ መንግስት ወደ እስር ቤት ያስገባሁት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው እና በወንጀል የተጠረጠሩት ብቻ ናቸው ቢልም ብዙዎች ከአስረኞች አያያዝ ጨምሮ አስሩ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም ያጠቃልላል የሚሉ ሀሳቦች በመነሳት ላይ ናቸው።
ሳዑዲ አረቢያ ብሔራዊ ቀኗን በማክበር ላይ ስትሆን በአዲስ አበባ የሚገኘው ኤምባሲዋ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት በዓሉን አክብሯል።
አል ዐይን አማርኛ በኢትዮጵያ የሳዑዲ አምባሳደር ሳሚ ቢን ጃሚል አብዱላህን በሳውዲ እስር ቤት ስላሉ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ጠይቋል።
አምባሳደሩ እንዳሉትም በሳውዲ እስር ቤት ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው የመመለሱ ሂደት በቅርቡ ይጠናቀቃል ብለዋል።
ሳዑዲ የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ (ኢቃማ) በትንሹ ከ3 ባልበለጡ ወራት ውስጥ እንዲታደስ ወሰነች
በእስር ቤት ያሉ እና ወደ አገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያንን በነጻ ወደ አገራቸው በመመለስ ላይ ነን ያሉት አምባሳደሩ በረራውን በሳዑዲ እና ኢትዮጵያ አየር መንገዶች በሳምንት ከ6 ጊዜ በላይ በረራዎችን እያካሄድን ነውም ብለዋል።
እስካሁን በተደረገው ጥረትም ከ45 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ብለዋል አምባሳደሩ።
እነዚህን ዜጎች ወደ አገራቸው የመመለሱ ተግባር እንደተጠናቀቀ አዲስ የስራ ቪዛ በሳዑዲ አረቢያ ከተሞች መስራት ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን መሰጠት ይጀመራልም ብለዋል።
በኢትዮጵያ በተለይም በግብርና እና ቱሪዝም ኢንቨስትመንት ከተሰማሩ የውጭ አገራት ኩባንያዎች መካከል የሳዑዲ ባለሀብቶች ቀዳሚዎቹ ናቸው።