አብደላ ሃምዶክ አሁንም የቤት ውስጥ እስረኛ ናቸው ተባለ
በሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራው የሃገሪቱ ጦር የመንግስት ግልበጣ አድርጎ ሌሎችንም ባለስልጣናት ማሰሩ ይታወሳል
ሃምዶክን ያሰረው የሃገሪቱ ጦር ለቋቸው እንደነበር ማስታወቁ ይታወሳል
በሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ልዩ መልዕክተኛ ባሳለፍነው ሰኞ ከሱዳን የሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ከተነሱት አብደላ ሃምዶክ ጋር መወያየታቸው ተገለጸ፡፡
ልዩ መልዕክተኛው በአብደላ ሃምዶክ መኖሪያ ቤት ተገኝተው ውይይት ማድረጋቸውን የገለጹ ሲሆን አሁንም የቤት ውስጥ እስረኛ ሆነው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
አብደላ ሃምዶክ አሁን ላይ በሙሉ ጤንነት ላይ ስለመሆናቸውም ነው ልዩ መልዕክተኛው የተናገሩት፡፡
በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተነሱት የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ከእስር ተለቀቁ
ቮከር ፔርዝስ፤ የሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው አብደላ ሃምዶክ አሁንም የቤት ውስጥ እሰረኛ መሆናቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ ያሰፈሩ ሲሆን ለሱዳን መፍትሄዎችን በጋራ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች ለሱዳን ይበጃሉ በተባሉ ቀጣይ መፍትሄዎችና የሽምግልና ሃሳቦች ላይ መነጋገራቸውን ልዩ መልዕክተኛው ተነጋግረዋል፡፡
ልዩ መልዕክተኛው ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለሱዳን ችግሮች መፍትሄ የመፈለጉን ስራ ማከናወናቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
የሱዳን ጦር፤ ትናንት ከቡርሃን የመከሩትን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክን ለምን አሰረ?
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክና የሲቪል መንግስቱ ባለስልጣናትን ከስልጣን ያነሱት የሱዳን ጦር አዛዥ አል ቡርሃን በሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ይታወሳል፡፡
ከዚህ ባለፈም፤ አል ቡርሃን በአሜሪካ፣ በአውሮፓ ህብረት እና በፈረንሳይ የሚገኙትን ጨምሮ በሌሎች ሀገራት የሚገኙ የሱዳን አምባሳደሮችን ከስራ ማባረራቸው አይዘነጋም፡፡
ዲፕሎማቶቹ የሱዳን የሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አብደላ ሃምዶክን በመደገፋቸው ከኃላፊነት መነሳታቸው መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡