“ሱዳን ከግልበጣው ጀምሮ በእስር ላይ ነው ያለችው”- መርየም አል ሳዲቅ፣ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ
መርየም ግልበጣውን አካሂደው በሲቪል ይመራ የነበረውን የሃገሪቱን መንግስት ካፈረሱት የጦር ጄነራሎች ጋር እንደማይደራደሩም ተናግረዋል
እርስበርስ ሊገናኙ የሚችሉበት መንገድ መዘጋቱን የተናገሩት መርየም አል ሰዲቅ “ሁላችንም በእስር ላይ ነን” ብለዋል
የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት መርየም አል ሳዲቅ “ሱዳን ከግልበጣው ጀምሮ በእስር ላይ ነው ያለችው” ሲሉ ተናገሩ፡፡
መርየም ግልበጣውን አካሂደው በሲቪል ይመራ የነበረውን የሃገሪቱን መንግስት ካፈረሱት የጦር ጄነራሎች ጋር እንደማይደራደሩም ተናግረዋል፡፡
በሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክን እና ሌሎች የካቢኔ አባላትን በቁጥጥር ስር በማዋል ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱ እና ሌሎች የሲቪል አደረጃጀቶች መፍረሳቸውን ያስታወቀው ከሳምንት በፊት ነበር ምንም እንኳን ሃምዶክን ከቀናት በኋላ ከእስር ቢለቅም፡፡
ግልበጣው በሽግግሩ የተስተዋሉ “ክፍተቶችን ለማረም” የተወሰደ “የማስተካከያ እርምጃ” ነው ሲሉ ቡርሃን መናገራቸው ይታወሳል፡፡
እርስበርስ ሊገናኙ የሚችሉበት መንገድ መዘጋቱን የተናገሩት መርየም አል ሰዲቅ “ሁላችንም በእስር ላይ ነን” ብለዋል፡፡
“ሃምዶክ አሁንም፤ ሱዳንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመምራት የመጀመሪያ እጩ ናቸው”- አል ቡርሃን
ከተቃዋሚው ዑማ ፓርቲ አመራሮች መካል አንዷ የሆኑት መርየም በጦሩ ካልታሰሩ ባለስልጣናት መካከል አንዷ ናቸው፡፡
መርየም በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ የሱዳን የመጨረሻው ጠቅላይ ሚኒስትር እንደነበሩ የሚነገርላቸው የታዋቂው ፖለቲከኛ አል ሳዲቅ አል ማህዲ ልጅ ናቸው፡፡
አል ማህዲ እ.ኤ.አ በ1989 በአል በሽር በተመራ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን መወገዳቸው ይታወሳል፡፡
ግልበጣውን ተከትሎ በሱዳን ተቃውሞው እና እስሩ ቀጥሏል፡፡ ለተቃውሞ ወደ አደባባዮች ከወጡት መካከል 11 ያህል ሰዎች መገደላቸውም ይነገራል፡፡
ሌ/ጄ አል-ቡርሃን በአሜሪካና አውሮፓ ህብረት የሚገኙትን ጨምሮ 6 የሱዳን አምባሳደሮችን ከስራ አባረሩ
አብደላ ሃምዶክን በጀግናነት ያወደሱት መርየም የወታደሩን እርምጃ “ክህደት ነው” ያሉት ሲሆን ወታደሩ በሚመሰርተው የትኛውም መንግስት ውስጥ እንደማይሳተፉ ገልጸዋል፡፡
“ከማንኞቹም ጋር ንግግር የለኝም አይኖረኝምም” ሲሉም ነው መርየም የተናገሩት፡፡
እውቀት ባላቸው ሰዎች የሚተዳደር መንግስት እንደሚመሰርቱ ያስታወቁት አል ቡርሃን መንግስት የመመስረቱ ሚና ለሃምዶክ ሊሰጥ እንደሚችል መናገራቸው ይታወሳል፡፡