በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን በጦሩ እና በጠ/ሚ ሃምዶክ የተደረሰውን ስምምነት በመቃወም አደባባይ ወጡ
በሃገሪቱ ብሔራዊ ቤተመንግስት አቅራቢያ ሰልፍ ያደረጉት ሱዳናውያኑ ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል
ሰልፈኞቹ ጦሩ ከሃገሪቱ ፖለቲካ እንዲገለል ጠይቀዋል
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን የሱዳን ጦር ከሃገሪቱ ፖለቲካ እንዲገለል ለመጠየቅ ወደ አደባባዮች ወጡ፡፡
ጦሩ አሁንም ከሃገሪቱ ፖለቲካ እጁን አልሰበሰበም ያሉት ሰልፈኞቹ ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 21/2013 በሃገሪቱ ቤተ መንግስት አቅራቢያ ሰልፍ አድርገዋል፡፡
አልቡርሃን በሱዳን እና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ጉብኝት አደረጉ
በጦሩ እና በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የተደረሰውንና ሃምዶክ ወደ ስልጣን እንዲመለሱ የተደረገበትን ስምምነት በመቃወም ነው ሰልፈኞቹ በናይል ወንዝ ዳርቻ ወደሚገኘው ቤተ መንግስት አቅራቢያ የተሰለፉት፡፡
ይዘዋቸው በወጡት መፈክሮችም የጦሩን ድርጊት አውግዘዋል፡፡ ስልጣን ለህዝብ ተላልፎ እንዲሰጥም ነው የጠየቁት፡፡ የሚደረግ “ስምምነትም ሆነ አጋርነት” እንደማይኖርም አስታውቀዋል፡፡
ሆኖም ሰልፉን በአስለቃሽ ጭስ ጭምር ለመበተን ጥረት ሲያደርግ ከነበረው የሃገሪቱ ፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡
በካርቱም ህዝባዊ ተቃውሞ መሪዎች ጥሪ የተሰባሰቡት ሰልፈኞቹ ተወግደው ወደነበሩበት ስልጣን የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በጦሩ ጣልቃ ገብነት ለተደናቀፈው የሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ የሽግግር ሂደት ቀጣይነት ዋስትና እንደሰጧቸው ጠይቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘረ እየተባለ የሚነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው ሲል መንግስት አስታወቀ
ሃምዶክ ወደ ስልጣናቸው ለመመለስ ከጦሩ መሪ ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር መስማማታቸው ይታወሳል፡፡
ሆኖም የሽግግር ሂደታችንን እየተደናቀፈ ነው ያሉትን ሱዳናውያንን አላሳመነም፡፡ ጦሩ ከፖለቲካው ገለል ብሎ በሲቪል የሚመራ ህዝባዊ መንግስት እንዲቋቋምም በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡