የዘመቻው የመጨረሻ ግብ የሆነችውን መቀሌን ለመያዝ እየገሠገሠ እንደሚገኝም ሠራዊቱ አስታውቋል
ሰራዊቱ እዳጋ ሐሙስን ተቆጣጠረ
የመከላከያ ሠራዊቱ ከአዲግራት ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ የምትገኘውን እዳጋ ሐሙስ ከተማን መቆጣጠሩን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡
ማጣሪያ ሰበር ሲል ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መረጃ የመከላከያ ሠራዊቱ የዘመቻው የመጨረሻ ግብ የሆነችውን መቀሌን ለመያዝ እየገሠገሠ ነው ብሏል።
ሠራዊቱ ከሰሞኑ ሽሬን፣ አክሱምን፣ አድዋንና አዲግራትን ነጻ ለማውጣት መቻሉንም አስታውሷል።
እዳጋ ሐሙስ በምስራቃዊ ትግራይ ወደ መቀሌ በሚዘልቀው አውራ ጎዳና ላይ ትገኛለች፡፡
ከባህር ጠለል በላይ እስከ 2700 ሜትር ያህል ድረስ ከፍ የምትልም ሲሆን ከመቀሌ በ98 ኪሎ ሜትሮች ትርቃለች፡፡
በመኪና ከእዳጋ ሐሙስ መቀሌ ለመድረስ 2 ገደማ ሰዓታትን ይወስዳል፡፡
ፍሬወይኒ (ሰንቃጣ)፣ ውቅሮ እና አጉላዕን የመሳሰሉ ከተሞች በእዳጋ ሐሙስ እና በመቀሌ መካከል ይገኛሉ፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ ከመቀሌ በ70 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ እንደሚገኝ በራያ ግንባር የሚዲያ አስተባባሪው ኮሎኔል ደጀኔ ጸጋዬ በኩል አስታውቆ ነበር፡፡
ይህ ምናልባት በቀጥታ ከእዳጋ ሃሙስ ሊሆን እንደማይችል ይገመታል፡፡