መንግስት እስረኞችን የፈታው ክስ አቋርጦ እንጅ በምህረትም፣በይቅርታም አለመሆኑን ገለጸ
እርምጃው የተወሰደው ሀገራዊ ምክክሩን አካታች ለማድረግ በማሰብ መሆኑን ገልጿል
መንግስት አቶ ስብሃት ነጋና አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ የተወሱ እስረኞችን በምህረት መልቀቁን አስታወቀ
የፌደራል መንግስት በባለደራልስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ መሪ አቶ እስክንድር ነጋ፣በፖለቲከኛ አቶ ጃዋር መሀመድ መዝገብ የነበሩ ሰዎችን የጨምሮ የህወሓት አመራሮችን የፈታው ክስ አቋርጦ መሆኑ ገለጸ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ትናንትና በሰጠው መግለጫ ይካሄዳል በተባለው ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ በማሰብ መንግስት እስተኞችን”በምህረት“ መፍታቱን ማስታወቁ ይታወሳል።
የፍትህ ሚኒስትር አቶ ጌዲዮን ጢሞቲዮስን ጠቅሶ ኢዜአ ዛሬ እንደዘገበው የመንግስት እስረኞችን የመፍታት እርምጃ በፍርድ ቤት ክርክር ሂደት ላይ የነበረን ክስ በማቋረጥ እንጂ በይቅርታም ወይም በምህረት አይደለም ብለዋል።
ሚኒስትሩ እርምጃው የተወሰደው ሀገራዊ ምክክሩን አካታች ለማድረግ በማሰብ መሆኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ሀገራዊ መግባባትና መስማማት የሚያስፈልጋቸው በርካታ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እስካሁን የተደረገ ሁሉን አቀፍ አገራዊ ምክክር አለመደረጉንና ሊካሄድ የታሰበው በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው አንደሚሆን ኢዜአ ዘግቧል።
ሚኒስትሩ እንዳሉት ከፖለቲካ ልሂቃን አልፈው ወደ ማህበረሰቡ እየተንጸባረቁ ያሉ ያለመግባባት ችግሮችን ለመፍታት ከመደበኛ ፍትህ በተጨማሪ እልባት መስጠት አስፈልጓል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ፣ ለተሻለ ፖለቲካዊ ምኅዳር ሲባል መንግስት የተወሰኑ እሥረኞችን በምሕረት ከእሥር መፍታቱን አስታውቋል።
ከእሥር በምሕረት እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ከህወሓት አመራሮች ውስጥ አቶ ስብሐት ነጋ፣ ወሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ ወሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር እና አቶ ኪሮስ ሐጎስ መሆናቸውንም ገልጿል።
በተጨማሪም አቶ ጁሐር መሐመድና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ እንዲሁም አቶ እስክንድር ነጋና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ ከእስር መልቀቀቁን ስታውቋል።