የትግራይ ክልል “የአማራ ክልል የትግራይ መሬቶችን በክልሉ ካርታ ላይ በማስፈር እያስተማረበት ይገኛል” ሲል ከሰሰ
የፌደራል መንግስት ችግሩን “አይቶ እንዳላየ ማለፉ የጥፋቱ አካል መሆኑን የሚያመላክት ነው” ነው ብሏል
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአማራ ክልል በመማሪያ መጽሐፍት ላይ ያወጣው ካርታ ላይ በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ አስጠንቅቋል
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአማራ ክልል መምንግስት “የትግራይ መሬቶችን በክልሉ ካርታ ላይ በማስፈር እያስተማረበት ይገኛል ሲል ከሰሰ።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫው፤ የአማራ ክልል መንግስት “የትግራይ መሬቶችን የግዛቱ አካል በማድረግ” በክልሉ ካርታ ላይ አስፍሯል ብሏል።
የትግራይ ክልል መሬቶች የሰፈሩበትን ካርታ በትምህርት ካሪኩለሙ በማካተት እያስተማረበት እንደሚገኝ ተረድቻለሁም ነው ያለው።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ የአማራ ክልል በመማሪያ መጽሐፍት ላይ ያውጣውየተሳሳተ ካርታ ላይ በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ አስጠንቅቋል።
ይህ የማይሆን ከሆነ ግን “ይህን ተከትሎ ለሚመጣው ነገር ሁሉ ሃላፊነቱን የሚወስደው የአማራ ክልል መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን” ብሏል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ በመግለጫው፤ የአማራ ክልል መንግስት ይህን ያደረገው “ሃላፊነት በጎደለው” መልኩ ብቻ ሳይሆን፤ “ትግራይን ቆራርሶ የማጥፋት ዘመቻ እንዳይቆም እና በከፋ መንገድ አሁንም እየሰራበት ስለመሆኑ ለመገንዘብ ችለናል” ሲል ገልጿል።
“የአማራ ክልል መንግስት በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸመው የመጣውን እና በጉልበት በተቆጣጠራቸው የትግራይ አከባቢዎች እየፈጸመው ያለው ግፍ እና መከራ እንዳይበቃ፤ በፈጸማቸው ጥፋቶች ሊጸጸት ሲገባው እንደዚህ አይነቱን ታሪካዊ ስህተት ውስጥ መግባቱ ዋጋ የሚያስከፍለው መሆኑን አውቆ በአፋጣኝ ሊያርመው ይገባል” ሲልም ግዚያው አስተዳደሩ አሰስቧል።
የፍደራል መንግስቱንም የተቸው የትግራይ ጊዜያው አስተዳደር፤ የፌደራል መንግስት በአማራ ክልል “ሃላፊነት በጎደለበት አኳኋን” በመዘጋጀት ያሉ ካርታዎች እንዲታረሙ ማድረግ እና አስፈላጊ እርምጃዎችንም መውሰድ ሲገባው “አይቶ እንዳላየ ማለፉ የጥፋቱ አካል መሆኑን የሚያመላክት ነው” የሚሆነው ሲል ገልጿል።
የፕሪቶርያው ስምምነት በተሟላ መልኩ በመፈጸም እየተሰባለበት ወቅት የአማራ ክልል መንግስት የዚህ አይነት ተግባር መፈጸሙ “የሰላም ሂደቱን ለማደፍረስ ሆን ብሎ የሚፈጽመው ጥፋት መሆኑ” ሊሰመርበት ይገባል ብሏል።