ፖለቲካ
ዶናልድ ትራምፕ፤ የአሜሪካ የጦር ጄቶች የቻይናን ሰንደቅ አላማ ይዘው ሩሲያን እንዲወጉ ሃሳብ አቀረቡ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናድ ትራምፕ ሩሲያን እንዴት ማንበርከክ እንደሚቻል ፍንጭ ሰጥተዋል
በዚህም ሩሲያና ቻይና ወደ ጦርነት ሲያመሩ አሜሪካ ቁጭ ብላ ታያለች ብለዋል
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያን እንዴት ማንበርከክ እንደሚቻል ፍንጭ ሰጡ።
የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየተካሄደ ባለው የሩሲያ እና ዩክሬን ጉዳይ ዙሪያ ንግግር አድርገዋል።
ትራምፕ እንዳሉት “ሩሲያን ለማሸነፍ የአሜሪካ የጦር ጀቶች የቻይናን ሰንደቅ አላማ ይዘው የሩሲያን የጦር ማዕከላት ሊያወድሙ ይገባል” ሲሉ መክረዋል።
በዚህም ምክንያት ሩሲያ እና ቻይና ወደ ጦርነት ያመራሉ ያሉት ዶናልድ ትራምፕ፤ ሁለቱ ሀገራት ሲዋጉ አሜሪካ ቁጭ ብላ ታያቸዋለች ሲሉም አክለዋል።
አሜሪካ በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እርምጃ መውሰድ እንደሌለባም ዶናልድ ትራምፕ ሃሳብ ሰጥተዋል።
ምዕራባውያን አሁን ላይ እየጣሉት ካለው ማዕቀብ አንጻር “እንደ ሽፍታ እየሆኑ ነው” ስትል ሩሲያ ክስ ማቅረቧ ይታወሳል።
በዩክሬን ጉዳይ የትኛወም የአውሮፓ አገር ቢሳተፍ የከፋ አደጋ ይጠብቀዋል ያሉት ፕሬዘዳንት ፑቲን የዩክሬን እቅዳቸው በሚፈልጉት መንገድ በመካሄድ ላይ መሆኑን መናገራውም አይዘነጋም።
በዛሬው እለትም ሩሲያ በወሰዱባት እርምጃ “ወዳጅ አይደሉም”ያለቻቸውን 48 ሃገራት ዝርዝር ይፋ ማድረጓ ይታወቃል።