ዩክሬናውያን ያላቸውን የኤሌትሮኒክስ መገልገያዎች በሙሉ ቻርጅ እንዲያደርጉ ሀገሪቱ አሳሰበች
በሩሲያ ጥቃት 30 በመቶ የዩክሬን የኃይል ማመንጫዎች መውደማቸውን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ገልጸዋል
የዩክሬን ኢነርጂ ኩባያ የሀገሪቱ ዜጎች ሙቀት ለማግኘት ወፍራም ልቦስን እንዲያዘጋጁና እርስ በእርስ እንዲተቃቀፉም አሳስቧል
የዩክሬን ብሄራዊ የኢነርጂ ኩባያ የሩሲያ የሚሰዔል ድብደባን ተከትሎ ለሚኖር የኤሌክትሪክ መቋረጥ የሀገሪቱ ዜጎች ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ሩሲያ በሳምንት ውስጥ በዩክሬን ላይ በሰነዘረችው ጥቃት 30 በመቶ የሀገሪቱ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን መውደማቸውን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ አስታውቀዋል።
ሩሲያ ኪቭን ጨምሮ በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች የወሰደችውን በድሮኖች የታገዘ እርምጃን ተከትሎ በሀገሪቱ የመብራት መቆራረጥና የውሃ አቅርቦት መቆራረጥ እንዳስከተለ ይነገራል።
ይህንን ተከትሎም የዩክሬን ብሄራዊ የኢነርጂ ኩባያ ለሚከሰት የኤሌክትሪክ ኃል መቆራረጥ ዩክሬናውያን ያላቸውን መገልገያዎች በሙሉ ቻርጅ እዲያደርጉ አሳስቧል።
ለሚኖረው የኤሌክትሪክኃል መቋረጥ ቅድመ ዝግጅትም ዩክሬናውያ ውሃ እንዲያከማቹ ያሳበው ባለስልጣኑ፤ ሙቀት የሚሰጡ ካልሲዎችን እና ብርድልብሶችን ኢንዲያዘጋጁ፤ እንዲሁም በቂ ሙቀት ለማግኘት ቤተሰቦች አሊያም ከጓደኞቻው ጋር እንዲተቃቀፉም አሳስቧል።
የሞባይል ስልኮች፣ ፓወር ባክኖች፣ የእጅ ባትሪዎች እና ሌሎች ቻርጅ የሚደረጉ ባትሪዎች እና መገልገያዎች በሙሉ ቻርጅ ተደርገው እንዲቀመጡም ኩባንያው አሳውቋል።
ሩሲያ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ የዩክሬን የኃይል መሰረት ልማቶችን እና ወታደራዊ ማእከሎችን ኢለማ ያደረገ ጥቃት በመሰንዘር ላጥ እንደሆነች ይታወቃል።
ሩሲያ ኪቭን ጨምሮ በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች የወሰደችውን በድሮኖች የታገዘ የእርምጃን ተከትሎ በሀገሪቱ የመብራት መቆራረጥና የውሃ አቅርቦት መቆራረጥ እንዳስከተለ ይነገራል።
ቢዘህም በኪቭ፣ በምስራቅ ካርኪቭ፣ በደቡብ እበዲኒፕሮ፣ ዞይቶሚር እና ማይኮላይቭ ግዛቶች የሚገኙ ሆስፒታሎች በመጠባበቂያ ጄነሬተሮች እየሰሩ መሆናቸውን ሮይተርስ የግዛቶቹን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል።