ሊማን ባለፉት ወራት የተነጠቀቻቸውን ግዛቶች ለመመለስ እየተዋጋች እንደሆነ ተነግሯል
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በሀገሪቱ ምስራቅ ግንባር ላይ ያለው ውጊያ እየጠነከረ መምጣቱን አስታውቀዋል።
ሩሲያ በርካታ ወታደሮችን ወደ ጦርነት እያሰማራች መሆኑንም ፐሬዚዳንቲ አስታውቀዋል። የሩሲያ ጦር ለወራት ካፈገፈገ በኋላ ጉልህ የሆነ የጦር ሜዳ ድል ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው ተብሏል።
የሩሲያ ጦር የባክሙት ከተማን ለመዝጋት እየሞከረ እና በአቅራቢያው ያለውን የዩክሬን ኃይል ለመቆጣጠር እየተዋጋ እንደሆነ ተነግሯል።
የሩስያ ወታደሮች ከባክሙት በስተደቡብ ምዕራብ 120 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የምትገኘውን የድንጋይ ከሰል ማውጫ ከተማ ቩሌዳርንና በምስራቅ የዲኔትስክ ግዛት ለመያዝ እየሞከሩ ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
"ብዙውን ጊዜ በግንባሩ ላይ ያለው ሁኔታ አስቸጋሪ ነው እያልኩ እናገራለሁ” ያሉት ፐሬዚዳንት ዘለንስኪ፤ “ያ ጊዜ እንደገና መጥቷል” ብለዋል።
'ወራሪው' መከላከያችንን ለማፍረስ ኃይሉን እየጨመረ ነው" ሲሉ ዘለንስኪ ተናግረዋል።
"አሁን በባክሙት፣ ቩሌዳር፣ ላይማን እና በሌሎች አቅጣጫዎች ያለው ሁኔታ በጣም ከባድ ነው" ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ወቅታዊ ውጊያውን ገልጸዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ቀደም ሲል ምክትል የመከላከያ ሚንስትር ሃና ማሊያር ሩሲያ በባክሙት እና በሊማን ያለውን መከላከያ ለመስበር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም ብለዋል።
ከባክሙት በስተሰሜን የምትገኘው ሊማን በጥቅምት ወር በዩክሬን ጦር ነጻ የወጣች ከተማ ናት።
በባክሙት ዙሪያ የተደረገው ጦርነት ከወታደሮች ህይወት አንጻር ለሩሲያ ብዙ ዋጋ ያስከፈለ መሆኑን ክሬምሊን አምኗል።