የጸጥታው ምክር ቤት ዛሬ በሱዳን ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ዝግ ስብሰባን ሊያደርግ ነው
ሆኖም ምክር ቤቱ በዝግ ስብሰባው ምንም እንኳ ግልበጣውን በጽኑ ሊያወግዝ ቢችልም ጠበቅ ያለ እርምጃን ለመውሰድ የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ አይጠበቅም ተብሏል
ስብሰባው በብሪታኒያ፣ በአየርላንድ፣ በኖርዌይ፣ በአሜሪካ፣ በኢስቶኒያ እና ፈረንሳይ ጥያቄ የሚደረግ ነው
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የጸጥታው ምክር ቤት ዛሬ በሱዳን ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል፡፡
ስብሰባው በዝግ የሚደረግ እንደሆነ ስለ ሁኔታው ቅርበት ያላቸው አምባሳደሮች ገልጸዋል፡፡
በብሪታኒያ፣ በአየርላንድ፣ በኖርዌይ፣ በአሜሪካ፣ በኢስቶኒያ እና ፈረንሳይ ጥያቄ ነው ስብሰባው ይደረጋል የተባለው፡፡
አሜሪካ ትናንት በሱዳን ያሉት ሁኔታዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደነበሩበት እንዲመለሱና በሃገሪቱ ጦር ቁጥጥር ስር በሚገኙት በጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክ የሚመራው የሲቪል መንግስት በመሪነቱ እንዲቀጥል ጠይቃለች፡፡
የሱዳን ጦር፤ ትናንት ከቡርሃን የመከሩትን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክን ለምን አሰረ?
የሱዳንን የሽግግር በኃይል መቀየር ታደርግ የነበረውን ድጋፍ እንደሚያሳጣ ደጋግማ ስታሳስብ የነበረችው ዋሽንግተን ለካርቱም ልታደርግ የነበረው የ700 ሚሊዮን ዶላር ርዳታ አቁማለች፡፡
ኒውዮርክ በሚገኘው የተመድ ዋና መስሪያ ቤት ለሚገኙ ጋዜጠኞች የበይነ መረብ መግለጫን የሰጡት በሱዳን የተመድ መልዕክተኛ ጀርመናዊው ቮከር ፐርዝ ስለተፈጠረው ሁኔታ ለምክር ቤቱ እንደሚያብራሩ ተናግረዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ድርጅቱ ሱዳንን የተመለከተ ውሳኔ ያሳልፋል ብለው መጠበቃቸውን ለዜናው ምንጭ የሆኑ ዲፕሎማቶች ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛዎች ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተልኩ ነው አለ
ሆኖም ምክር ቤቱ ምንም እንኳን ግልበጣውን በጽኑ ሊያወግዝ ቢችልም በዚህ ጉዳይ ሊገፋበት እንደማይችል ዲፕሎማቶቹ ጠቁመዋል፡፡
ትናንት በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች የሚተገበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን ያስታወቀውና በሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን፣ ካቢኔውን እንደ አጠቃላይ የሲቪል መንግስቱን መበተኑን ገልጿል፡፡
ይህን ተከትሎ ጦሩ ዓለም አቀፍ ውግዘቶችን እያስተናገደ ነው፡፡ የታሰሩት በአስቸኳይ ሊለቀቁ ይገባል ያለው ተመድም ድርጊቱን አውግዟል፡፡
ግልበጣውን ተከትሎ በሱዳን የኢንተርኔትና ሌሎች ግንኙነቶች ተቋርጠዋል፡፡