ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ 3ኛው ዙር የውኃ ሙሌት አጠናቀቀች
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የዓባይ ወንዝ ዘንድሮ ከ600 ሜትር ከፍታ ላይ ሞልቶ መፍሰሱን ገልጸዋል
ዘንድሮ 22 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ገደማ ውሃ መያዝ የሚያስችል ስራ መሰራቱን ጠ/ሚ ዐቢይ ትናንት አስታውቀዋል
የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሶስተኛው ዙር ሙሌት ተጠናቀቀ።
የአባይ ውሃ ለሦስተኛ ጊዜ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አናት ላይ መፍሰስ መጀመሩን አል ዐይን ኒውስ ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የግድቡን ሙሌት በስኬት ማብሰሪያ ላይ ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የግድቡን 3ኛ ዙር ሙሌት መጠናቀቅ አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር፤ አባይ ከባሕር ጠለል በላይ ከ600 ሜትር ከፍታ ላይ መፍሰስ ጀምሯል ብለዋል።
አምና ውሃው ሞልቶ ሲፈስ የግድቡ የመሃልኛው ክፍል ከፍታ 575 ሜትር ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ዘንድሮ ከ600 ሜትር ከፍታ ላይ ሞልቶ መፍሰሱን ገልጸዋል።
የግራ እና ቀኝ የግድቡ ከፍታም አምና 585 ሜትር እንደነበረ እና ዘንሮ ላይ 611 ሜትር ላይ መድረሱን አስታውቀዋል።
የግድቡ ሙሌት ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 70 ገደማ ደሴቶች አንደሚኖሩት ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፤ 40 ያህሉ ከ10 ሄክታር በላይ ይሸፍናሉ ብለዋል።
“ሪዞርት ብናደርጋቸው አሳ ብናረባ ብዙ እንጠቀማለን” ያሉ ሲሆን፤ “ዓለም መጥቶ ለመዝናናት የሚያስችለው ትልቅ ስጦታ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
“ሶስቱ ሃገራት በነጻ ለመጠቀም የተሳጣቸውን መጠቀምና መተባበር አለባቸው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “በሚገባቸው ድርሻ መጠቀም የማያምኑ ከተፈጥሮ ህግ እየተቃረኑ መሆኑን ይወቁት” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትናትነው እለት በተካሄደው የሃይል ማመንጨት ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ዘንድሮ 22 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ገደማ ውሃ መያዝ የሚያስችል ስራ መሰራን አስታውቀዋል።
“ሆኖም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራተ ላይ የውሃ እጥረት እንዳያግጥም ኢነርጂ እያመነጨን በታቸኛው ቦተም አውት ሌት በኩል ውኃ በከፍተኛ ሁኔታ አንድም ቀን ሳይቋረጥ እንዲሄድ እየተደረገ ነው” በለዋል።
“የሚፈሰውን ውሃ ብንይዝ ኖሮ በአጠረ ጊዜ ውስጥ ውሃ መሙላት ይቻል ነበረ ነገር ግን የኛ ፍላጎት የመልማት ብ መሆኑን ለማሳየት ውሃ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት እየለቀቀች ነው” ብለዋል።
“በረዘመ ጊዜ ውስጥ ውጃ የምንሞላው የታችኛው ተፋሰስ ሀጋርተ ሳይጎዱ እኛም ሳንጎዳ በጋራ ለመልማት ያለንን ፍላጎት ተረድተው በንግግር እና በድርድር ውጤት እንደሚመጣ እንዲተጉ” ጥሪ አቅርበዋል።