አሜሪካ ዲፕሎማቶቿን ወደ ዩክሬን ልትመልስ ነው
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚኒስትሮች በባቡር ወደ ኪቭ ተጉዘው ከሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ጋር መወያየታቸው ይታወሳል
ብሪታኒያ በአጭር ጊዜ ውስጥ የኪቭ ኤምባሲዋን እንደምትከፍት ማስታወቋ የሚታወስ ነው
አሜሪካ ከሩሲያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ከዩክሬን ያስወጣቻቸውን ዲፕሎማቶች በዚህ ሳምንት ወደ ኪቭ እንደምትመልስ አስታወቀች፡፡
ዲፕሎማቶቹ በምዕራባዊ ዩክሬን ለቪቭ ከተማ በኩል አድርገው ወደ ኪቭ እንደሚገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን አስታውቀዋል፡፡ ይህ ምናልባትም ዘለግ ያለ ጊዜን ሊወስድ እንደሚችልም ነው ብሊንከን የገለጹት፡፡
ብሊንከን ከመከላከያ ሚኒስትሩ ሊሎድ ኦስቲን ጋር በመሆን ከሰሞኑ ዩክሬንን ጨምሮ በፖላንድ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ከፖላንድ ወደ ኪቭ ሲሄዱም ሲመለሱም በድምሩ 22 ሰዓታትን የፈጀ የባቡር ጉዞ አድርገውም ከፕሬዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ውይይቱ ሶስት ሰዓታትን የፈጀ ነው፡፡ ዩክሬን በሚያስፈልጓት ድጋፎች ዙሪያ ያተኮረ ነበርም ተብሎለታል፡፡
በሩሲያ ላይ የተጣሉ ማእቀቦችን የማንሳት ጉዳይ ከዩክሬን ጋር የሚደረገው ድርድር አንድ አካል ነው - ላቭሮቭ
በአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ የተመራ የኮንግረስ አባላት ልዑክም ዛሬ ኪቭን ጎብኝቷል፡፡
ልዑኩ በኪቭ ከፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ጋር የተወያየ ሲሆን በቀጣይ ወደ ፖላንድ አቅንቶ ከፕሬዝዳንት አንድሬ ዱዳ ጋር እንደሚወያይም አስታውቋል፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን በስሎቫኪያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑትን ብሪጌት ብሪንክን የዩክሬን አምባሳደር አድርገው ስለመሾማቸውም ነው የተነገረው፡፡
ጥቂት የማይባሉ የአውሮፓ ህብረት እና የኔቶ አባል ሃገራት ዲፕሎማቶቻቸውን ወደ ኪቭ እየመለሱ ነው፡፡ የብሪታኒያ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ የኪቭ ኤምባሲውን እንደሚከፍት ማስታወቁም የሚታወስ ነው፡፡
ጉቴሬዝ እየጎበኟት ያሉት የዩክሬኗ መዲና ኪቭ በሮኬት ተመታች
የዲፕሎማቶቹ መመለስ ዩክሬን ወራትን ባስቆጠረው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት ቢደርስባትም መሻሻል እያሳየች ለመምጣቷ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡